Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 66 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አስር ረከዓዎችን ሸምድጃለሁ። እነርሱም ከዙህር በፊት ሁለት ረከዓ፣ ከዙህር በኋላም ሁለት ረከዓ፣ ከመግሪብ በኋላ ቤታቸው ውስጥ ሁለት ረከዓ፣ ከዒሻእ በኋላም ቤታቸው ውስጥ ሁለት ረከዓ፣ ከሱብሒ ሶላት በፊት ሁለት ረከዓ ናቸው። የሱብሒ ወቅት ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ የማይገባባት ሰአት ነበረች። ስለሰአቲቱም ሙአዚኑ አዛን ያለ ጊዜና ጎህ የወጣ ጊዜ ሁለት ረከዓ ይሰግዱ እንደነበር ሐፍሷ ነገረችኝ።" በሌላ ዘገባ ደግሞ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጁመዓ ሶላት በኋላም ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር።"
ሶሒሕ ነው። በሁሉም ዘገባዎቹ ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል።
‹አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ: 'አልላሁምመፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲከ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ለኔ የእዝነትህን በሮች ክፈትልኝ) ይበል። የወጣ ጊዜም ‘አልላሁምመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! እኔ ከትሩፋትህ እጠይቅሀለሁ።) ይበል።›"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሶላትን የረሳ ሰው ባስታወሰው ጊዜ ይስገድ። ከዚህ በቀር ማካካሻ የለውም። {ሶላትንም (በርሷ) እኔን ለማስታወስ ስገድ።} [ጣሀ:14]
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«የጁመዓ ቀን ልክ እንደ ጀናባ ትጥበት ከታጠበ በኃላ ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የግመል ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በሁለተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የከብት ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በሶስተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ ቀንዳም ሙክት ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በአራተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የዶሮ ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በአምስተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የእንቁላል ቁርባን እንዳቀረበ ነው። ኢማሙ ለኹጥባ የወጣ ጊዜ መላእክቶቹም ተግሳፁን ለመስማት ይገኛሉ።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ዑሥማን ቢን ዐፋን (የነቢዩን) መስጂድ መገንባት ፈለጉ። ይህንንም ሰዎች ጠሉ። ባለበት እንዲተወውም ፈለጉ። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: 'የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: ‹ ለአላህ ብሎ መስጂድን የገነባ አላህም ለርሱ አምሳያውን ጀነት ውስጥ ይገነባለታል።›' አለ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሰዎች ጁመዓዎችን ከመተው ይከልከሉ! አለበለዚያ ግን አላህ በልቦቻቸው ላይ ያሽጋል። ከዚያም ከዝንጉዎች ይሆናሉ።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሰዎች በአዛንና በመጀመሪያ ሰልፍ ያለውን ምንዳ ቢያውቁና እርሱንም እጣ ካልተጣጣሉ በቀር የማያገኙት ቢሆን ኖሮ እጣ ይጣጣሉ ነበር። (ወደ መስጊድ) ማልዶ የመሄድን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ ለርሱ ይሽቀዳደሙ ነበር። የዒሻና ሱብሒን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳኹም ቢሆን ይመጡ ነበር።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"በሰባት አጥንቶቼ ሱጁድ እንዳደርግ ታዝዣለሁ። በግንባሬ በማለት በእጃቸው ወደ አፍንጫቸው አመላከቱ፣ በሁለቱ እጆቼ፣ በሁለቱ ጉልበቴ፣ በሁለቱ እግር ጣቶቼ ፤ ልብሳችንንም ይሁን (ለወንዶች) ፀጉራችንን እንዳንሰበስብም ታዘናል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።