Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 5 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የሴት ልጅ አለባበስን የሚለብስን ወንድና የወንድ ልጅ አለባበስን የምትለብስ ሴትን ረገሙ።"
ሶሒሕ ነው። ነሳኢይ በ "አል-ኩብራ" በተሰኘው ኪታባቸው፣ ኢብኑ ማጃህ በተመሳሳይ ትርጉም እና ኢማም አሕመድ ዘግበውታል
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሐር በግራ እጃቸው ወርቅ በቀኝ እጃቸው በመያዝ ከዚያም እነሱን በእጃቸው ከፍ አደረጉና እንዲህ አሉ: "እነዚህ ሁለቱ ከኡመቴ በወንዶቹ ላይ ክልክል ናቸው። ለሴቶቹ ግን የተፈቀደ ነው።"»
ሶሒሕ ነው። አቡ ዳውድ፣ ነሳኢይ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል
"ለርሱ ሁለት ሚስቶች ኑረውት ወደ አንዳቸው የተዘነበለ የትንሳኤ ቀን ጎኑ የተንሻፈፈ ሆኖ ይመጣል።"
ሶሒሕ ነው። አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚይ፣ ነሳኢይ፣ ኢብኑ ማጃህ እና አሕመድ ዘግበውታል
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ የጉዳይ ጊዜ ኹጥባን (ኹጥበቱል ሓጃህ) አስተማሩን: 'ኢነልሐምደ ሊላህ ነስተዒኑሁ ወነስተጝፊሩሁ ወነዑዙ ቢላሂ ሚን ሹሩሪ አንፉሲና ፤ መን የህዲላሁ ፈላሙዺለ ለሁ ወመንዩዽሊል ፈላ ሃዲየ ለሁ ፤ ወአሽሀዱ አን ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአሽሀዱ አነ ሙሓመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ ሱረቱ ኒሳእ: 1፣ ኣሊ‐ዒምራን: 102፣ አል‐አሕዛብ: 70‐71'" (ትርጉሙም: ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው። እገዛን ከርሱ እንፈልጋለን። ምህረትንም ከርሱ እንፈልጋለን። ከነፍሳችን ክፋትም በርሱ እንጠበቃለን። አላህ የመራው ሰው አጥማሚ የለውም። ያጠመመውንም መሪ የለውም። ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ። ሙሐመድም የአላህ ባሪያውና መልክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ። {እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን (ሐዋን) የፈጠረውን ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ። ያንንም በርሱ የምትጠያየቁበትን አላህንና ዝምድናዎችንም (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ። አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና።} [አንኒሳእ: 1] {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢውን መጠንቀቅ ተጠንቀቁት። እናንተም ሙስሊሞች ሆናችሁ እንጂ አትሙቱ።} [አሉ ዒምራን: 102] {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ። ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ። [70] ሥራዎቻችሁን ለእናንተ ያበጅላችኋልና ሀጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምርላችኋል። አላህንና መልክተኛውን የሚታዘዝም ሰው በእርግጥ ታላቅን እድል አገኘ። [71]} [አልአሕዛብ 70 -71])
ሶሒሕ ነው። አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚይ፣ ነሳኢይ፣ ኢብኑ ማጃህ እና አሕመድ ዘግበውታል
«ነቢዩን ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቃል ልንጋባ ከተወሰኑ የአንሷር ሴቶች ጋር ሆኜ መጣሁ። እንዲህም አልናቸው: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በአላህ ላይ አንዳችንም ላናጋራ፤ ላንሰርቅ፤ ዝሙትን ላንሰራ፤ በእጆቻችንና በእግሮቻችን መካከል የምንቀጥፈውን ቅጥፈት ላንፈፅም፤ በመልካም ጉዳይም ላናምፅዎት ቃል እንጋባዎ" እርሳቸውም: "በቻላችሁት ጉዳዮችና አቅማችሁ በሚፈቅደው ጉዳዮች ቃል ተጋባኃችሁ!" አሉን። እኛም "አላህና መልክተኛው ለኛ የበለጠ አዛኝ ናቸው። የአላህ መልክተኛ ሆይ! ኑ እጅዎን ይዘርጉ ቃል እንጋባዎ።" አልን። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "እኔ ሴቶችን አልጨብጥም። ለመቶ ሴቶች የምናገረው ቃል ለአንዲ ሴት እንደምናገረው ነው። ወይም ልክ ለአንድ ሴት እንደምናገረው ነው።" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚይ፣ ነሳኢይ እና ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል