"አንዳችሁ የበላ ጊዜ በቀኙ ይብላ። የጠጣም ጊዜ በቀኙ ይጠጣ። ሰይጣን የሚበላውም በግራው፤ የሚጠጣውም በግራው ነውና።"
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:
"አንዳችሁ የበላ ጊዜ በቀኙ ይብላ። የጠጣም ጊዜ በቀኙ ይጠጣ። ሰይጣን የሚበላውም በግራው፤ የሚጠጣውም በግራው ነውና።"
«إِذَا أَكَلَ أَحَدُكُمْ فَلْيَأْكُلْ بِيَمِينِهِ، وَإِذَا شَرِبَ فَلْيَشْرَبْ بِيَمِينِهِ، فَإِنَّ الشَّيْطَانَ يَأْكُلُ بِشِمَالِهِ، وَيَشْرَبُ بِشِمَالِهِ».
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ሙስሊም ሲበላም ሆነ ሲጠጣ በቀኝ እጁ እንዲሆን አዘዙ። በግራው ከመብላትና ከመጠጣትም ከለከሉ። ይህም ሰይጣን የሚበላውም ሆነ የሚጠጣው በግራው ስለሆነ ነው።
በግራ በመብላት ወይም በመጠጣት ከሰይጣን ጋር ከመመሳሰል መከልከሉን እንረዳለን።
ሶሒሕ ሙስሊም (3/ 1598) (2020).
ተጨማሪ (8)
توضيح الأحكام مِن بلوغ المرام.
للبسام (5/ 445).
فتح ذي الجلال والإكرام شرح بلوغ المرام.
لابن عثيمين (6/ 270).
سبل السلام شرح بلوغ المرام.
للصنعاني (2/ 625).
عون المعبود شرح سنن أبي داود (10/ 179).
فتاوى اللجنة الدائمة - المجموعة الأولى- (26/ 387).