Skip to content

በአይሁድ እና ክርስቲያኖች ላይ የአላህ እርግማን ይውረድ ! የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው ያዙ።

ከእናትችን ዓኢሻና ዐብደላህ ቢን ዓባስ - (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦

"የሞት መልዐክ በአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ የወረደ ጊዜ ፊታቸው ላይ ጨርቃቸውን ጣል ማድረግ ጀመሩ ፤ ሲያፍናቸው ደግሞ ይገልጧት ነበር ፤ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ 'በአይሁድ እና ክርስቲያኖች ላይ የአላህ እርግማን ይውረድ ! የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው ያዙ።' አሉ፤ ይህም ከሰሩት ስራ እያስጠነቀቁ ነው። '"

لَمَّا نَزَلَ بِرَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ طَفِقَ يَطْرَحُ خَمِيصَةً لَهُ عَلَى وَجْهِهِ، فَإِذَا اغْتَمَّ بِهَا كَشَفَهَا عَنْ وَجْهِهِ، فَقَالَ وَهُوَ كَذَلِكَ: «لَعْنَةُ اللَّهِ عَلَى اليَهُودِ وَالنَّصَارَى، اتَّخَذُوا قُبُورَ أَنْبِيَائِهِمْ مَسَاجِدَ» يُحَذِّرُ مَا صَنَعُوا.

ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

እናታችን ዓኢሻና ኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሞት የቀረባቸው ጊዜ የጨርቅ ቁራጭ ፊታቸው ላይ ጣል ያደርጉ እንደነበርና በሞት ስካር ሳቢያ ለመተንፈስ ያስቸገራቸው ጊዜም ከፊታቸው ያስወግዱት እንደነበር ነገረችን። በዚህ ከባድ ሁኔታ ላይ እያሉ አላህ አይሁድና ክርስቲያኖችን እንደረገመ፤ ከእዝነቱም እንዳራቀ፤ ይህም በነቢያቶቻቸው መቃብር ላይ መስገጃ በመገንባታቸው ምክንያት መሆኑን ነገረችን። የጉዳዩ አደገኛነት ከባድ ባልነበር በእንደዚ አይነት ሁኔታ ላይ ሆነው አይጠቅሱትም ነበር። ስለዚህም ይህ የአይሁዶችና ክርስቲያኖች ድርጊት በአላህ ላይ ወደ ማጋራት የሚያዳርስ ነውና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ መሰል ድርጊቶች ላይ ከነርሱ ጋር መመሳሰልን ከለከሉ።

የቃላት ፍቺ

.....:

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

የነቢያቶችንና ደጋጎችን መቃብር ለአላህ የሚሰገድበት መስገጃ አድርጎ መያዝ ወደ ሺርክ የሚያዳርስ ስለሆነ መከልከሉን እንረዳለን።

የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በተውሒድ ላይ ያላቸው ትኩረትና ጥንቃቄ የበረታ መሆኑንና መቃብርን ማላቅም ወደ ሺርክ ስለሚያዳርስ መስጋታቸውን እንረዳለን።

አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን መርገም እንዲሁም ቀብር ላይ በመገንባትና መቃብርን መስገጃ አድርጎ በመያዝ የነርሱን ድርጊት አምሳያ የሰራን ሰውም መርገም እንደሚፈቀድ እንረዳለን።

በመቃብር ላይ መገንባት የአይሁዶችና ክርስቲያኖች ሱና መሆኑንና ሐዲሡ ከነርሱ ጋር መመሳሰልንም ይከለክላል።

መስገጃ ባይገነባበት እንኳ እርሱ ዘንድ መስገድና ወደርሱ ዙሮ መስገድ መቃብርን መስገጃ አድርጎ መያዝ ውስጥ ይካተታል።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ አልቡኻሪ (1/ 95) (435).

(2/ 102) (1390).

ሶሒሕ ሙስሊም (1/ 377) (531).

(1/ 376) (529).

ተጨማሪ (4)

الملخص في شرح كتاب التوحيد.

للشيخ صالح الفوزان (ص170).

الجديد في شرح كتاب التوحيد.

لمحمد بن عبد العزيز السليمان القرعاوي (ص185).