Skip to content

"አንድ ሰው በታመመ ወይም ጉዞ በወጣ ወቅት ሀገሩ እያለና ጤናማ ሳለ እንደሚያደርገው አጅር ይጻፍለታል።"

ከአቡ ሙሳ አል-አሽዓሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡

"አንድ ሰው በታመመ ወይም ጉዞ በወጣ ወቅት ሀገሩ እያለና ጤናማ ሳለ እንደሚያደርገው አጅር ይጻፍለታል።"

«إِذَا مَرِضَ الْعَبْدُ أَوْ سَافَرَ كُتِبَ لَهُ مِثْلُ مَا كَانَ يَعْمَلُ مُقِيمًا صَحِيحًا».

ቡኻሪ ዘግበውታል።
ሶሒሕ ነው።
ማብራሪያ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለአሏህ እዝነትና ችሮታ እየነገሩን ነው። ይህም አንድ ሙስሊም በሀገሩ እና ጤነኛ ሳለ ልምድ ያደረገው መልካም ስራ ከዚያም ችግር ገጥሞት ታሞ ማድረግ ባይችል፣ ወይም በጉዞ ወይም ደግሞ በሌላ በየትኛውም በቂ ምክንያት ሳያደርገው ቢቀር ልክ ጤነኛና በሀገሩ ሆኖ ሲያደርግ እንደነበረው ምንዳ ሙሉ ሆኖ ይጻፍለታል።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

አሏህ በባሮቹ ላይ ያለው ችሮታ ስፋቱን እንረዳለን።

ጤነኛ በሆንን እና ትርፍ ጊዜ ባገኘንበት አጋጣሚ መልካም ተግባርና ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም መበርታት እንደሚገባን እንረዳለን።

ማጣቀሻዎች

ሶሒሕ አልቡኻሪ (4/ 57) (2996).

ተጨማሪ (6)

شرح رياض الصالحين.

لابن عثيمين (1/ 36).

بهجة الناظرين شرح رياض الصالحين.

لسليم الهلالي (1/ 211).

بهجة قلوب الأبرار وقرة عيون الأخيار في شرح جوامع الأخبار.

لعبد الرحمن السعدي (ص83).