Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 16 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
'በኛና በነርሱ (በከሀዲዎች) መካከል ያለው (መለያ) ቃል ኪዳን ሶላት ነው። ሶላትን የተወ ሰው በርግጥም ክዷል።'"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ፣ ነሳኢ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"'የገድ እምነት ሺርክ ነው። የገድ እምነት ሺርክ ነው። የገድ እምነት ሺርክ ነው። ከኛ መካከል አንድም የለም በልቡ የገድ እምነት የሚመጣበት ቢሆን እንጂ። ነገር ግን አላህ በርሱ ላይ በመመካታችን ምክንያት ያስወግደዋል።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
'ከአሏህ ውጭ ባለ አካል የማለ ከፍሯል ወይም አጋርቷል።'"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"የኮኮብ እውቀትን (በትንሹም) የቀሰመ ሰው ከፊልን ጥንቆላ ቀስሟል። (የኮኮብ እውቀት መቅሰሙን) በጨመረ ቁጥር (ጥንቆላውም) ይጨምራል።'"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሑደይቢያ ምሽት የዘነበን ዝናብ አስከትለው የንጋትን (የሱብሒን) ሰላት አሰገዱን። ሰላቱን ያጠናቀቁ ጊዜም ወደ ሰዎች በመዞር እንዲህ አሉ "ጌታችሁ ምን እንዳለ ታውቃላችሁን?" ሰሓቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ" አሉ። እርሳቸውም አላህ እንዲህ አለ፦ "ከባሮቼ በኔ ያመነም የካደም ሆኖ ያነጋ አለ። በአላህ ችሮታና እዝነት ምክንያት ዘነበልን ያለ በኔ ያመነ በከዋክብት የካደ ነው። በእንዲህ እንዲህ የኮኮብ እንቅስቃሴ ምክንያት ዘነበልን ያለ ደግሞ በኔ የካደና በከዋክብት ያመነ ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"በአሏህ ሳያጋራ አሏህን የተገናኘ ጀነት ገብቷል፤ እያጋራበት አሏህን የተገናኘ ደግሞ እሳት ገብቷል።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ ሆይ! ኢብኑ ጁድዓን በጃሂሊያ (በድንቁርናው)ዘመን ዝምድናን የሚቀጥልና ሚስኪኖችን የሚመግብ ነበር። ይህ ይጠቅመዋልን?" አልኳቸው። እሳቸውም "አንድ ቀንም "ጌታዬ ሆይ! የምንዳው ቀን ወንጀሎቼን ማረኝ" ብሎ ስለማያውቅ አይጠቅመውም።" አሉ።
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባዱ ሶላት የዒሻእ ሶላትና የፈጅር ሶላት ናቸው። በውስጧ ያለውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን ይመጡ ነበር። በርግጥ ሶላት እንዲሰገድ አዝዤ፤ ሰዎችን እንዲያሰግድም አንድ ሰው ላዝ፤ ከዚያም ሶላትን በመስጂድ ተገኝተው ወደማይሰግዱ ሰዎች ቤት የታሰረ እንጨት ከያዙ ወንዶች ጋር በመሄድ በነሱ ላይ ቤቶቻቸውን በእሳት ላቃጥል አስቤም ነበር።'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።