Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 36 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
እውነተኛና (ይዘውት በመጡትም ሁሉ) እውነተኛ የተባሉት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (ይህንን) ነገሩን፦ "የአንዳችሁ ፍጥረት በእናቱ ሆድ ውስጥ ለአርባ ቀንና ምሽት ይሰበሰባል። ከዚያም የዛኑ ቀናት አምሳያ የረጋ ደም ይሆናል፤ ከዚያም የዛኑ ቀናት አምሳያ ቁራጭ ስጋ ይሆናል፤ ከዚያም ወደርሱ መልዐክ ይላካል ፤ መልዐኩ አራት መልእክቶች ይታዘዛል፤ ሲሳዩን፣ የሞት ቀጠሮውን፣ ስራውንና እድለቢስ ወይም እድለኛ መሆኑን ይጽፋል። ከዚያም በውስጡ ነፍስ ይነፋበታል። አንዳችሁ በርሱና በጀነት መካከል የክንድ ያህል ርቀት እስኪቀር ድረስ የጀነት ሰዎችን ስራ ይሰራል። በርሱ ላይ የተጻፈው መጽሐፉ (ውሳኔ) ይቀድምና የእሳት ባለቤቶችን ስራ ይሰራና እሳት ይገባል። አንዳችሁ በርሱና በእሳት መካከል የክንድ ያህል ርቀት እስኪቀር ድረስ የእሳት ሰዎችን ስራ ይሰራል። በርሱ ላይ የተጻፈው መጽሐፉ (ወሳኔ) ይቀድምና የጀነት ባለቤቶችን ስራ ይሰራና ጀነት ይገባል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«አንድ ፀጉሩ የተበታተነ የነጅድ ነዋሪ የሆነ ሰው ወደ አላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣ፤ ወደ አላህ መልእክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እስኪቀርቡ ድረስ ከፍ ያለ ድምፁን እንሰማ ነበር ነገር ግን የሚናገረውን ልንረዳው አልቻልንም፤ ለካ ስለ እስልምና እየጠየቀ ኖሯል። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሲመልሱለት "በቀንና በምሽት የሚሰገድ አምስት ሶላቶች ነው።" አሉት። እርሱም "ከነዚህ ሶላቶች በቀር ሌላ ሶላት አለብኝን?" አላቸው። እርሳቸውም "አይ በፍቃደኝነት (የምተሰግደው ሶላት) ካልሆነ በቀር ሌላ የለብህም። እንዲሁም የረመዳንን ወር መጾም።" አሉት። እርሱም "ከዚህ ጾም በቀር ሌላ ጾም አለብኝን?" አላቸው። እርሳቸውም "አይ በፍቃደኝነት (የምትጾመው ጾም) ካልሆነ በቀር ሌላ የለብህም።" አሉት። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘካንም አወሱለት። እርሱም "ከዚህ ውጪ ሌላ የምፅዋት ግዴታ አለብኝን?" አላቸው። እርሳቸውም "አይ በፈቃደኝነት (የምትመፀውተው) ካልሆነ በቀር ሌላ የለብህም።" አሉት። ሰውዬውም "በአላህ እምላለሁ! ከዚህ አልጨምርምም አልቀንስምም።" እያለ ዞሮ ሄደ። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "እውነቱን ከተናገረ ስኬታማ ሆነ!" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
'ከአሏህ ውጭ ባለ አካል የማለ ከፍሯል ወይም አጋርቷል።'"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"ከዚህ በፊት አብዝተው ነፍስ የሚገድሉ፣ አብዝተው ዝሙት የሚሰሩ የነበሩ የሺርክ ባለቤት የሆኑ ሰዎች ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በመምጣት እንዲህ አሉ ' የምትናገረውና የምትጣራበት ጉዳይ መልካም ነው። ለሰራነው ፀያፍ ተግባር ማስማሪያ እንዳለው እንደው ብትነግረን?' {እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይግገዙት፤ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ህግ የማይገድሉት፤ የማያመነዝሩትም ናቸው።} [ፉርቃን:68] የሚለውና {በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ።»} [አዝዙመር: 53] የሚለው አንቀፅ ወረደች።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የኮኮብ እውቀትን (በትንሹም) የቀሰመ ሰው ከፊልን ጥንቆላ ቀስሟል። (የኮኮብ እውቀት መቅሰሙን) በጨመረ ቁጥር (ጥንቆላውም) ይጨምራል።'"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሑደይቢያ ምሽት የዘነበን ዝናብ አስከትለው የንጋትን (የሱብሒን) ሰላት አሰገዱን። ሰላቱን ያጠናቀቁ ጊዜም ወደ ሰዎች በመዞር እንዲህ አሉ "ጌታችሁ ምን እንዳለ ታውቃላችሁን?" ሰሓቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ" አሉ። እርሳቸውም አላህ እንዲህ አለ፦ "ከባሮቼ በኔ ያመነም የካደም ሆኖ ያነጋ አለ። በአላህ ችሮታና እዝነት ምክንያት ዘነበልን ያለ በኔ ያመነ በከዋክብት የካደ ነው። በእንዲህ እንዲህ የኮኮብ እንቅስቃሴ ምክንያት ዘነበልን ያለ ደግሞ በኔ የካደና በከዋክብት ያመነ ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
“አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ፡- " የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ (ከእርሶ መላክ በፊት ባለው የድንቁርና ዘመን) በሠራነው ሥራ እንቀጣለን?" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉት፡- "በኢስላም ሥራውን ያሳመረ፥ በጃሂሊያ በሠራው ሥራ ተጠያቂ አይሆንም። እስልምናን ተቀብሎም መጥፎ የሠራ ግን በቀድሞውም በኋለኛውም ስራው ይጠየቅበታል። "
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"በአሏህ ሳያጋራ አሏህን የተገናኘ ጀነት ገብቷል፤ እያጋራበት አሏህን የተገናኘ ደግሞ እሳት ገብቷል።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።