Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 36 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"አራት (ባሕርያት) በእርሱ ላይ ያለበት ሰው ሙናፊቅ ሆኗል፤ ከአራቱ ባህሪዎች ውስጥ አንዱ ያለበት ደግሞ እስኪተዋት ድረስ አንድ የሙናፊቅነት ባህሪ ይኖረዋል፦ ሲናገር ይዋሻል፤ ቀጠሮ የያዘ ጊዜ ያፈርሳል፤ ሲከራከር ወሰን ያልፋል፤ ቃልኪዳን ከገባ በኋላ ቃልኪዳኑን ይክዳል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
"ሰይጣን አንዳችሁ ዘንድ በመምጣት "ይህን የፈጠረው ማነው? ይህንንስ የፈጠረው?" እያለ ይጠይቃችኋል "ጌታህንስ የፈጠረው ማነው?" ብሎ እስኪጠይቃችሁ ድረስ ይደርሳል፤ ይህ ጥያቄ የደረሰው ጊዜ በአላህ ይጠበቅም ይከልከልም።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"(በአማና) በአደራ የማለ ሰው ከኛ አይደለም።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሙዐዝ ቢን ጀበልን ወደ የመን በሚልኩበት ጊዜ እንዲህ አሉት፡ ' አንተ የመጽሐፍ ባለቤት ወደሆኑ ህዝቦች ትሄዳለህ። ስለዚህም እነርሱ ዘንድ ስትደርስ ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን ወደ መመስከር ጥሪ አድርግላቸው። እነሱ ለዚህ ጥሪህ ታዛዥ ከሆኑ አሏህ በነሱ ላይ በቀንና ምሽቱ ሁሉ አምስት ሶላቶችን ግዴታ እንዳደረገባቸው አሳውቃቸው። ለዚህ ጥሪህም ታዛዥ ከሆኑ አላህ በነሱ ላይ ከሀብታሞቻቸው ተይዞ ወደ ድሆቻቸው የምትሰጥ ምፅዋት ግዴታ እንዳደረገባቸው አሳውቃቸው። ለዚህ ጥሪህም ታዛዦች ከሆኑ አደራህን ውድ የሆኑ ንብረቶቻቸውን (ገንዘቦቻቸውን) ተጠንቀቅ! የተበዳይንም ልመና ተጠንቀቅ! እነሆ በሷና በአላህ መሀል ግርዶሽ የለምና።'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"በሰዎች ውስጥ ሁለት ነገሮች አሉ፤ እነርሱም ክህደት ናቸው። በዘር መተቸትና በሞተ ላይ ሙሾ ማውረድ ናቸው።"»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህ አማኝን አንድም መልካም ሥራውን አይበድለውም በዱንያ በሷ ምክንያት (መልካም ነገር) ሲሰጠው በአኺራም በሷ ምክንያት ይመነዳዋል። ካፊር ግን ለአላህ ብሎ በሠራው መልካም ሥራ ምክንያት በዱንያ እንዲበላ ይደረጋል። ወደ አኺራ የተሸጋገረ ጊዜ በአኺራ የሚመነዳበት መልካም ሥራ አይኖረውም።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«እስልምና በአምስት መሰረቶች ተገነባ እነርሱም: 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛ ናቸው።) ብሎ መመስከር፣ ሶላትን ማቋቋም፣ ዘካ መስጠት፣ በተከበረው የአሏህ ቤት ሐጅ ማድረግ እና የረመዷንን ወር መፆም ናቸው።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የሙናፊቅ ምሳሌው በሁለት (የፍየል) መንጎች መካከል እንደዋለለች ፍየል ነው። አንድ ጊዜ ወደ አንዱ ሌላ ጊዜም ወደ ሌላኛው ትሄዳለች።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።