Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 19 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"የወንድሙን ክብር በመንካት ወይም በአንዳች ነገር ወንድሙን የበደለ ሰው ዲናርና ዲርሃም የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ዛሬ ከራሱ ላይ በደሉን ያስነሳ። (የትንሳኤ ቀን) መልካም ስራ ካለው በበደሉ ልክ ይቀነስበታል። ለርሱ መልካም ስራ ከሌለው ከበደለው ባልደረባው ወንጀሎች ተወስደው እርሱ ላይ ይደረጋሉ።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
"የጀነት ነዋሪ ማን እንደሆነ አልነግራችሁምን? ደካማ፣ ዝቅ የሚደረግ፣ በአላህ ላይ ቢምል ግን አላህ መሃላውን እውን የሚያደርግለት የሆነ ሁሉ ነው። የእሳት ነዋሪስ ማን እንደሆነ አልነግራችሁምን? ልበ ደረቅ፣ ትዕቢተኛና በኩራት የተሞላ ነው።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የትንሳኤ ቀን ፀሐይ ወደ ፍጡራን የአንድ ሚል (ማይል) ያህል ትቀርባለች።" ሱለይም ቢን ዓሚርም እንዲህ አለ "በአላህ እምላለሁ! እርሳቸው ሚል በማለት የፈለጉት የምድር ርቀት መለኪያውን ይሁን ወይስ ዐይን መኳያ እቃውን ይሁን ምን እንደፈለጉበት አላውቅም።" ነቢዩ እንዲህም ብለዋል "ሰዎችም እነደየስራቸው መጠን በላብ ይጠመቃሉ። ከነርሱ መካከል ላቡ እስከቁርጭምጭሚቱ ድረስ የሚሆን አለ፤ ከነርሱ መካከል እስከጉልበቱ ድረስ የሚሆን አለ፤ ከነርሱ መካከል እስከመታጠቂያው ድረስ የሚሆንም አለ፤ ከነርሱ መካከልም ላቡ የሚለጉመው አለ።" ብለው የአላህም መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በእጃቸው ወደአፋቸው ጠቆሙ።»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«ጀነት ውስጥ የአንዳችሁ ትንሹ ደረጃ አላህ ለርሱ "ተመኝ" ይለዋል። እርሱም ደጋግሞ ይመኛል። አላህም ለርሱ "ተመኘህን?" ይለዋል። እርሱም "አዎን" ይላል። አላህም ይለዋል: "ላንተ የተመኘኸውንም ከርሱም ጋር የርሱን አምሳያ ሌላም ይሰጥሃል።"»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ ነበርን። የ14ኛዋን ሌሊት ጨረቃ ተመለከቱና እንዲህ አሉ: ' ይህን ጨረቃ እንደምትመለከቱት ጌታችሁንም በርግጥ ታያላችሁ። እርሱን ለማየትም ምንም አትቸገሩም። ፀሀይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት ባለው ሶላት ላይ አለመሸነፍን ከቻላቹ አድርጉት።' ቀጥሎ ይህንን አንቀፅ አነበቡ: '{ጌታህንም ከማመስገን ጋር ፀሀይ ከመውጣቷ በፊት ከመግባቷም በፊት አወድሰው።}'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የወርቅና የብር ባለቤት ሆኖ ሐቃቸውን የማይወጣ ሰው የትንሳኤ ቀን ለርሱ የእሳት ዝርግ ተዘርግቶለት በርሷ በጀሃነም እሳት ውስጥ ሳይቃጠል የሚቀር የለም። ጎኑም፣ ግንባሩና ጀርባውም የሚተኮስ መሆኑ አይቀርም።" በቀዘቀዘች ቁጥር እየተመላለሰች መጠኑ ሀምሳ ሺህ አመት የሚያህል ለሆነ ቀን ይተኮሳል። ይህም በባሮች መካከል ፍርድ ተፈርዶ መንገዱ ወደ ጀነት ወይስ ወደ እሳት ነው የሚለውን እስኪመለከት ድረስ የሚዘልቅ ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የትንሳኤ ቀን የትኛውም ባሪያ እድሜውን በምን እንዳጠፋው፣ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘውና ምን ላይ እንዳዋለው፣ በአካሉ ምን እንዳደረገበት ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም።'"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ ዘግበውታል።
{ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ።} [አትተካሡር: 8] የሚለው አንቀፅ የወረደ ጊዜ ዙበይር እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እንመገብ የነበረው ሁለቱን ጥቁሮች ተምርና ውሃ ነው። ስለማንኛው ድሎት ነው የምንጠየቀው?" እሳቸውም "እርሱኑ ሳይሆን አይቀርም የምትጠየቁት።" አሉት።
ሐሰን ነው። ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።