Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 13 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ። በናንተ ውስጥ የመርየም ልጅ ፍትሃዊ ዳኛ በቅርቡ ሆኖ ይወርዳል። መስቀልን ይሰባብራል፣ አሳማን ይገድላል፣ ግብርን ያነሳል፣ አንድም ሰው እስከማይቀበለው ድረስም ገንዘብ (ሀብት) ይበዛል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሙስሊም ቀብር ውስጥ በተጠየቀ ጊዜ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ይመሰክራል።" ይህም አላህ እንዲህ እንዳለው ነው: {አላህ እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቱም ህይወት በመጨረሻይቱም (በመቃብር) በተረጋገጠው ቃል ላይ ያረጋቸዋል።} [ኢብራሂም:27]
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ዘመኑ እስኪጣበብ ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም። አመቱ እንደ ወር ይሆናል፤ ወሩ እንደ ሳምንት ይሆናል፤ ሳምንቱም እንደ ቀን ይሆናል፤ ቀኑም እንደ ሰአት ይሆናል፣ ሰአቱም የተምር ዛፍ (ዘንባባ) ቅጠል እንደሚቃጠልበት ጊዜ (ያጠረ) ይሆናል።"
ሶሒሕ ነው። አሕመድ ዘግበውታል።
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አንድ ነገር ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ይህ የሚከሰተውም ዕውቀት ሊጠፋ የቀረበ ጊዜ ነው።" እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ ቁርኣን እየቀራን ፣ ልጆቻችንን እያቀራን፣ ልጆቻችንም ልጆቻቸውን እስከ እለተ ትንሳኤ እያቀሩ እንዴት ዕውቀት ይጠፋል?" አልኳቸው። እሳቸውም "እናትህ ትጣህ! ዚያድ በመዲና ጥልቅ ግንዛቤ ያለህ አድርጌ አይህ ነበርኩ። እነዚህ አይሁድና ክርስቲያን ተውራትና ኢንጂልን እየቀሩ ውስጣቸው ያለውን ምንም የማይሠሩ አይደሉምን?!" አሉኝ።
በሌላ ሰነድ ታግዞ ሶሒሕ ነው። ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።
"ጀናዛ (ሬሳ) ቃሬዛ ላይ የተቀመጠች ጊዜና ሰዎች ትከሻቸው ላይ የተሸከሟት ጊዜ ሬሳዋ መልካም ከሆነች "ቀደም አድርጉኝ!" ትላለች። መልካም ካልሆነች ደግሞ "ወዬውላት የት ነው ይዛችኋት የምትሄዱት?" ትላለች። ከሰው በቀር ያለ ነገር ሁሉ ድምጿን ይሰማል። የሰው ልጅ ቢሰማው ኖሮ ራሱን ስቶ ይወድቅ ነበር።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።