Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 24 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
'አላህ ምድርን በጭብጡ ያደርጋል፤ ሰማያትንም በቀኝ እጁ ይጠቀልልና ከዚያም ‹እኔ ነኝ ንጉሱ! የምድር ነገስታት የት አሉ?!› ይላል።'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"እናንተ ሰዎች ሆይ! አላህ መልካም (ጥሩ) ነውና ከመልካም (ከጥሩ) በቀር አይቀበልም። አላህ መልክተኞችን ባዘዘው ነገር አማኞችንም አዟል። አላህ እንዲህ ብሏል: {እናንተ መልክተኞች ሆይ! ከተፈቀዱት ምግቦች ብሉ። በጎ ስራንም ስሩ። እኔ የምትሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነኝ።} [አልሙእሚኑን:51] እንዲህም ብሏል: {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከነዚያ ከሰጠናችሁ ጣፋጮችን ብሉ።} [አልበቀራህ: 172]" ቀጥለውም ጉዞ የሚያረዝም፣ ጨብራራ፣ ፊቱንና ልብሱን አቧራ ያለበሰው አንድ ሰውዬ አወሱ። እጁን ወደ ሰማይ እየዘረጋ: "ጌታዬ ሆይ! ጌታዬ ሆይ! እያለ ይለምናል። ምግቡ ሐራም ነው። መጠጡ ሐራም ነው። ልብሱ ሐራም ነው። በሐራም ነው የተገነባው። እንዴት ለርሱ ዱዓው ተቀባይነት ይኖረዋል?" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«አላህ አንድን ባሪያ የወደደው ጊዜ ጂብሪልን ይጠራውና እንዲህ ይለዋል: "እኔ እከሌን እወደዋለሁና ውደደው።" ጂብሪልም ይወደዋል። ቀጥሎ ጂብሪል ሰማይ ውስጥ እንዲህ በማለት ይጣራል: "አላህ እከሌን ይወደዋልና ውደዱት።" የሰማይ ነዋሪዎችም ይወዱታል። ከዚያም ምድር ላይ ተቀባይነት ይኖረዋል። አላህ አንድን ባሪያ የጠላ ጊዜም ጂብሪልን በመጥራት እንዲህ ይለዋል: "እኔ እከሌን እጠላዋለሁና ጥላው።" ጂብሪልም ይጠላዋል። ቀጥሎም ጂብሪል ለሰማይ ነዋሪዎች እንዲህ በማለት ይጣራል: "አላህ እከሌን ይጠላዋልና ጥሉት።" እነርሱም ይጠሉታል። ከዚያም ምድር ላይ ተጠይነትን ይኖርበታል።»
ሶሒሕ ነው። ሶሒሕ ሙስሊም
'አላህ በዳይን ያዘገየዋል። የያዘው ጊዜ ግን አይለቀውም!'" አቡ ሙሳ እንዲህ አለ: "ቀጥለውም {የጌታህም ቅጣት የከተሞችን ሰዎች እነሱ በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው ጊዜ እንደዚህ ነው። ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚ ብርቱ ነው።} [ሁድ: 102] የሚለውን አነበቡ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "አላህ እንዲህ አለ: የአደም ልጅ አስተባበለኝ ይህ ለርሱ አይገባም ነበር! ሰደበኝም ይህም ለርሱ አይገባም ነበር! እኔን ማስተባበሉማ ‹መጀመሪያ እንደፈጠረኝ (የትንሳኤ ቀን) አይመልሰኝም› ማለቱ ነው። በኔ ላይ እርሱን (የትንሳኤ ቀን) ከመመለስ ይልቅ መጀመሪያ መፍጠሩ ቀላል አይደለምን?። እኔን መስደቡማ ‹አላህ ልጅን ያዘ!› ማለቱ ነው። እኔ አንድ ነኝ፣ የሁሉ መጠጊያም ነኝ፣ አልወልድም፣ አልወለድም፣ ለኔም አንድም ቢጤ የለኝም።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
" አንድ ባሪያ የአንድን ባሪያ ነውር በዱንያ አይሸፍንም፤ የትንሳኤ ቀን አላህ ነውሩን የሚሸፍንለት ቢሆን እንጂ።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል "አላህ እንዲህ አለ: እኔ ባሪያዬ ባሰበኝ በኩል ነኝ። ባስታወሰኝም ጊዜ እኔ ከርሱ ጋር ነኝ። ለብቻው ካወሳኝ ለብቻዬ አወሳዋለሁ፤ በህብረት ካወሳኝ ደሞ ከርሱ የተሻለ በሆኑ ህብረቶች ዘንድ አወሳዋለሁ። አንድ ስንዝር ወደኔ ከቀረበ አንድ ክንድ ወደርሱ እቀርባለሁ። አንድ ክንድ ወደኔ ከቀረበ እጅ ሙሉ ወደርሱ እቀርባለሁ። እየተራመደ ወደኔ ከመጣ በሶምሶማ ወደርሱ እመጣለሁ።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የላቀውና ከፍ ያለው ጌታችን በሁሉም ሌሊት የመጨረሻ ሲሶ ሲቀር ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል። እንዲህም ይላል 'ማን ነው የሚለምነኝ የምመልስለት? ማን ነው የሚጠይቀኝ ለርሱ የምሰጠው? ማን ነው ምህረትን ከኔ የሚፈልገው ለርሱ የምምረው?'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።