Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 20 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
‹አላህ ይቀናል። አማኝ የሆነ ሰውም ይቀናል። የአላህ መቅናት ሰውዬው አላህ በሱ ላይ ክልክል ያደረገበትን ሲዳፈር ነው።›"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደነገሩን አንድ ሰው "የአላህ ነቢይ ሆይ! ከሓዲዎች በትንሣኤ ቀን እንዴት በፊቶቻቸው እየተሳቡ ይቀሰቀሳሉ?" አላቸው። እርሳቸውም " ያ በዱንያ ውስጥ እያሉ በሁለት እግራቸው እንዲሄዱ ያደረጋቸው የትንሳኤ ቀን በፊታቸው እንዲሄዱ ማድረግ የሚችል አይደለምን?" አሉት። ቀታዳህ እንዲህ አሉ፦ "በጌታዬ ልቅና ይሁንብኝ እንዴታ!"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህ አማኝን አንድም መልካም ሥራውን አይበድለውም በዱንያ በሷ ምክንያት (መልካም ነገር) ሲሰጠው በአኺራም በሷ ምክንያት ይመነዳዋል። ካፊር ግን ለአላህ ብሎ በሠራው መልካም ሥራ ምክንያት በዱንያ እንዲበላ ይደረጋል። ወደ አኺራ የተሸጋገረ ጊዜ በአኺራ የሚመነዳበት መልካም ሥራ አይኖረውም።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስፍራ መስጂዶች ናቸው። አላህ ዘንድ እጅግ የሚጠላው ስፍራ ገበያዎች ናቸው።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህ ተባረከ ወተዓላ ለጀነት ነዋሪዎች እንዲህ ይላቸዋል: 'እናንተ የጀነት ነዋሪዎች ሆይ!' እነርሱም 'ደጋግመን በደስተኝነት አቤት ብለናል' ይላሉ። አላህም 'ተደሰታችሁን?' ይላቸዋል። እነርሱም 'ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካል ያልሰጠኸውን ሰጥተኸን እንዴት ነው የማንደሰተው?' ይላሉ። እርሱም 'እኔ ከዚህም የተሻለ ነገር እሰጣችኋለሁ።' ይላል። እነርሱም 'ጌታችን ሆይ! ከዚህ የተሻለ ምን አይነት ነገር ይኖራል?' ይላሉ። አላህም 'በናንተ ላይ ውዴታዬን አሰፍናለሁ። በናንተ ላይ ከዚህ በኋላ መቼም አልቆጣም።' ይላቸዋል።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሚዛናዊ ሁኑ፤ በተቻለ መጠን ወደ እሱ ቅርብ ለመሆን ሞክሩ ከናንተ መካከል አንድም ሰው በስራው እንደማይድንም እወቁ!" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርሶም ቢሆኑ በስራዎት አይድኑምን?" አሉ። እርሳቸውም "አላህ ከርሱ በሆነ እዝነትና ችሮታ ካልሸፈነኝ በቀር እኔም ብሆን በስራዬ አልድንም።" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህ ወደ ቅርፃችሁና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ስራዎቻችሁ ይመለከታል።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ከናንተ መካከል በርሱና በአላህ መካከል አስተርጓሚ ሳይኖር አላህ የሚያናግረው ቢሆን እንጂ አንድም ሰው የለም ወደ ቀኝ ይመለከታል። ያሳለፈውን እንጂ ሌላ ምንም አይመለከትም። ወደ ግራም ይመለከታል ካሳለፈው በቀር ሌላ ምንም አይመለከትም። ከፊትለፊቱ ይመለከታል በፊትለፊቱ ከእሳት ውጭ ሌላ ምንም አይመለከትም። በተምር ክፋይ እንኳ ቢሆን እሳትን ተጠንቀቁ።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።