Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 28 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ኋላ ዑፈይር የሚባለው አህያ ላይ ተፈናጥጬ ሳለው "ሙዓዝ ሆይ አላህ በባሮቹ ላይ ያለውን ሐቅ፤ ባሮችስ አላህ ዘንድ ያላቸውን ሐቅ ታውቃለህን? " አሉ። "አላህና መልክተኛው ይወቁ !" አልኩኝ። እሳቸውም "አላህ በባሮቹ ላይ ያለው ሐቅ ሊገዙትና በሱ ላይም አንዳችንም ላያጋሩ ሲሆን፤ ባሮች አላህ ዘንድ ያላቸው ሐቅ ደግሞ በሱ ላይ አንዳችንም ያላጋራን ላይቀጣ ነው።" አሉ። "የአላህ መልክተኛ ሆይ ሰዎችን ላበስራቸውን?" አልኳቸው። እሳቸውም "አታበስራቸው (በዚህ ስራ ላይ ብቻ) ይደገፋሉ (ይሳነፋሉ)። " አሉ።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
'ላኢላሃ ኢለሏህ ብሎ ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ነገሮች የካደ ሰው ገንዘቡም ደሙም እርም ይሆናል። ሂሳቡ ያለው አላህ ላይ ነው።'"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የቂያማ ቀን በርሶ ምልጃ ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ እድለኛው ማን ነው?" ተባሉ። የአላህ መልክተኛም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፡- 'አቡ ሁረይራ ሆይ! ባንተ ላይ ካየሁት የሐዲሥ ጉጉት አንፃር ይህንን ጥያቄ ለመጠየቅ የሚቀድምህ አይኖርም ብዬ አስቤ ነበር። የቂያማ ቀን በኔ አማላጅነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ እድለኛ የሚሆኑት ጥርት ባለ መልኩ ከልባቸው ወይም ከነፍሳቸው 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ያሉት ናቸው።'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
"ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ ለኔ እንዲህ አለኝ: 'የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በላኩኝ ነገር ላይ ልላክህን? ማንኛውም ምስልን (ስታገኝ) ያስወገድከው ቢሆን እንጂ ላትተወው ነው፤ ማንኛውም ከፍ ያለ ቀብርንም ያስተካከልከው ቢሆን እንጂ ላትተወው ነው።'"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"በጣዖታትም ሆነ በአባቶቻችሁ አትማሉ።"»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድ ተሰባስበን ተቀምጠን ነበር። ከኛ ጋር ከነበሩት መካከልም አቡበከርና ዑመር ነበሩ። የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከመካከላችን ተነስተው ሄዱ። ወደ እኛ ሳይመለሱም ዘገዩ። ከኛ ርቀው ባሉበት ጥቃት ይደርስባቸዋል ብለን በመፍራታችንም ደንግጠን ቆምን። ደንግጨ የተነሳሁት የመጀመሪያ ሰው እኔ ነበርኩኝ። የአላህ መልክተኛን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ለመፈለግም ወጣሁ። በመፈለግ ሳለሁም ባለቤትነቱ ከአንሷሮች መካከል ለአንድ የበኒ ነጃር ተወላጅ የሆነ የአትክልት ግቢ ጋር ደረስኩ። የመግቢያ በሩን ለማግኘትም አጥሩን ዞርኩት። በሩንም አላገኘሁም። ድንገት ግን ከግቢ ውጪ ከሚገኝ ጉድጓድ ወደ አትክልቱ ግቢ ውስጥ የሚገባ ቦይ አገኘሁ። ሰውነቴን ሸምቅቄ የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድ ገባሁ። እርሳቸውም "አቡ ሁረይራ" አሉኝ። እኔም "አቤት የአላህ መልክተኛ ሆይ!" አልኳቸው። "ምን ሆነህ ነው?" አሉኝ። እኔም "እርሶ በመካከላችን ነበሩ። ከመካከላችን ተነስተው ሄዱና ዘገዩብን። ከኛ ርቀው ባሉበት ጥቃት እንዳይደርስቦት ፈርተን ደነገጥን። መጀመሪያ የደነገጠውም ሰው እኔ ነበርኩኝ። ይህ የአትክልት ግቢ ዘንድ መጣሁ። ቀበሮ ሰውነቱን ሸምቅቆ እንደሚገባውም ሰውነቴን ሸምቅቄ ገባሁ። የተቀሩት እርሶን የሚፈልጉ ሰዎች ከኋላዬ ናቸው።" አልኳቸው። እርሳቸውም "አቡ ሁረይራ ሆይ! … " አሉኝና ሁለት ጫማቸውን ሰጥተው እንዲህ አሉኝ "እነዚህን ሁለት ጫማዎቼን ያዝና ሂድ! ከዚህ የአትክልት ግቢ ውጪ የምታገኘውን ላኢላሃ ኢለሏህን ከልቡ አምኖበት የሚመሰክርን ሰው በጀነት አበስረው።" መጀመሪያ ያገኘሁትም ዑመርን ነበር። እርሱም "ምንድናቸው እነዚህ ጫማዎች?" አለኝ። እኔም "እነዚህ የረሱል ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጫማዎች ናቸው። እነዚህን ጫማዎች ሰጥተው ከአጥሩ ውጭ ያገኘሁትን ላኢላሃ ኢለሏህን ከልቡ አምኖ የሚመሰክርን ሰው በጀነት እንዳበስረው ልከውኝ ነው።" አልኩኝ። ዑመርም በሁለት እጆቹ ደረቴን መታኝና በመቀመጫዬ ወደቅኩ። እንዲህም አለኝ "ተመለስ አንተ አቡ ሁረይራ" እኔም ወደ አላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንባ እየተናነቀኝ ተመለስኩኝ። ዑመርም ከኋላየ ነበር ሳስተውልም እኔን ተከትሎ መጥቷል። የአላህ መልክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ምን ሆንክ አንተ አቡ ሁረይራ!" አሉኝ። እኔም "ዑመርን አገኘሁት። የላኩኝን ጉዳይም ስነግረው ደረቴ ላይ መቶኝ በመቀመጫዬ ወደቅኩ። ተመለስም አለኝ።" አልኳቸው። የአላህ መልክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "አንተ ዑመር ለዚህ ተግባርህ ምን አነሳሳህ?!" አሉት። እርሱም "እናትና አባቴ ለርሶ ፊዳ ይሁኑና የአላህ መልክተኛ ሆይ! አቡ ሁረይራን ላኢላሃ ኢለሏህን ከልቡ አምኖበት የሚመሰክር ሆኖ ያገኘውን ሰው በጀነት እንዲያበስር ልከውታልን?" አለ። እርሳቸውም "አዎ" አሉ። እርሱም "እንዲህ አያድርጉ። ሰዎች በርሷ ላይ ጥገኛ ይሆናሉ (ይሳነፋሉ) ብዬ እፈራለሁ። ተዉዋቸው ይስሩ።" አለ። የአላህ መልክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ተዉዋቸው (አትንገሯቸው)" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
እርሱ በአንድ ጉዞ ላይ ከአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር ነበርና እንዲህ አለ: "ሰዎች በማደሪያቸው ባሉበት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (ይህንን የሚያውጅ) አንድ መልክተኛ ላኩ ' በግመል አንገት ላይ (የታሰረ) የቀስት ገመድ ወይም ገመድ የተቆረጠ ቢሆን እንጂ ምንም እንዳይቀር!'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ኡሙ ሰላማ ለአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሀበሻ ምድር ማሪያህ በምትባል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላየቻቸው ምስሎች ነገረቻቸው። የአላህ መልዕክተኛም ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፡- "እነዚህ ከመካከላቸው መልካም (ጻድቅ) ባርያ ወይም መልካም ሰው ሲሞት በመቃብሩ ላይ መስገጃን የሚገነቡና በውስጡም (ምስሉን) ስእላ ስእል የሚቀርፁ ናቸው። እነዚህ ህዝቦች አላህ ዘንድ እጅግ ክፉ (መጥፎ) ፍጡራን ናቸው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።