Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 9 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ሰልፋችሁን አስተካክሉ! ሰልፍ ማስተካከል ሶላትን ከሚሞሉት መካከል ነውና።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስፍራ መስጂዶች ናቸው። አላህ ዘንድ እጅግ የሚጠላው ስፍራ ገበያዎች ናቸው።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«እኛ ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ተቀምጠን ሳለ ድንገት አንድ የገጠር ሰው መጣና መስጂድ ውስጥ መሽናት ጀመረ። የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ባልደረቦችም "አተ! አተ!" አሉት። የአላህ መልክተኛም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "አታቋርጡት ተዉት!" አሉ። ሸንቶ እስኪያጠናቅቅም ተዉት። ቀጥሎ የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጠሩትና እንዲህ አሉት: "እነዚህ መስጂዶች ለዚህ ሽንትና ቆሻሻ አይበጁም። እነዚህ የሚበጁት አላህን ለማውሳት፣ ለሶላትና ቁርአንን ለመቅራት ነው።" አሉት። ወይም የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ይህን የመሰለ ንግግር ተናገሩት። አንድን ሰው ውሃ የሞላ ባልዲ ይዞ እንዲመጣ አዘዙና እላዩ ላይ ደፉበት።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
‹አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ: 'አልላሁምመፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲከ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ለኔ የእዝነትህን በሮች ክፈትልኝ) ይበል። የወጣ ጊዜም ‘አልላሁምመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! እኔ ከትሩፋትህ እጠይቅሀለሁ።) ይበል።›"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ዑሥማን ቢን ዐፋን (የነቢዩን) መስጂድ መገንባት ፈለጉ። ይህንንም ሰዎች ጠሉ። ባለበት እንዲተወውም ፈለጉ። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: 'የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: ‹ ለአላህ ብሎ መስጂድን የገነባ አላህም ለርሱ አምሳያውን ጀነት ውስጥ ይገነባለታል።›' አለ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓ ይስገድ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ኡሙ ሰላማ ለአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሀበሻ ምድር ማሪያህ በምትባል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላየቻቸው ምስሎች ነገረቻቸው። የአላህ መልዕክተኛም ሶለላሁ ​​ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፡- "እነዚህ ከመካከላቸው መልካም (ጻድቅ) ባርያ ወይም መልካም ሰው ሲሞት በመቃብሩ ላይ መስገጃን የሚገነቡና በውስጡም (ምስሉን) ስእላ ስእል የሚቀርፁ ናቸው። እነዚህ ህዝቦች አላህ ዘንድ እጅግ ክፉ (መጥፎ) ፍጡራን ናቸው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"በዚህ መስጂዴ የሚሰገድ ሶላት ከርሱ ውጪ ከሚሰገዱ አንድ ሺህ ሶላቶች የተሻለ ነው። የተከበረው መስጊድ (መስጂደል ሐራም) ሲቀር።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።