Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 50 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ዘመኑ እስኪጣበብ ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም። አመቱ እንደ ወር ይሆናል፤ ወሩ እንደ ሳምንት ይሆናል፤ ሳምንቱም እንደ ቀን ይሆናል፤ ቀኑም እንደ ሰአት ይሆናል፣ ሰአቱም የተምር ዛፍ (ዘንባባ) ቅጠል እንደሚቃጠልበት ጊዜ (ያጠረ) ይሆናል።"
ሶሒሕ ነው። አሕመድ ዘግበውታል።
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አንድ ነገር ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ይህ የሚከሰተውም ዕውቀት ሊጠፋ የቀረበ ጊዜ ነው።" እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ ቁርኣን እየቀራን ፣ ልጆቻችንን እያቀራን፣ ልጆቻችንም ልጆቻቸውን እስከ እለተ ትንሳኤ እያቀሩ እንዴት ዕውቀት ይጠፋል?" አልኳቸው። እሳቸውም "እናትህ ትጣህ! ዚያድ በመዲና ጥልቅ ግንዛቤ ያለህ አድርጌ አይህ ነበርኩ። እነዚህ አይሁድና ክርስቲያን ተውራትና ኢንጂልን እየቀሩ ውስጣቸው ያለውን ምንም የማይሠሩ አይደሉምን?!" አሉኝ።
በሌላ ሰነድ ታግዞ ሶሒሕ ነው። ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።
"አዛን ባዩን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አምሳያ በሉ። ከዚያም በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ። እነሆ በኔ ላይ አንዲትን ሶላት ያወረደ በርሱ ምክንያት አላህ በርሱ ላይ አስር ሶለዋት ያወርድለታል። ከዚያም ለኔ ከአላህ ወሲላን ጠይቁልኝ። እርሷም ጀነት ውስጥ ያለች ደረጃ ናት። ከአላህ ባሮች መካከል ለአንድ ባሪያ እንጂ ለሌላ አትገባም። እርሱም እኔ እሆናለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ወሲላን ለኔ የጠየቀልኝ ሰው ለርሱ ምልጃዬ ትፀናለታለች።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሰዎች የትንሳኤ ቀን ባዶ እግራቸውን፣ ራቁትና ያልተገረዙ ሆነው ይሰበሰባሉ።" እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ወንዶችም ሴቶችም ባጠቃላይ ከፊሉ ወደ ከፊሉ እየተመለከተ?" አልኳቸው። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "ዓኢሻህ ሆይ! ጉዳዩኮ ከፊሉ ወደ ከፊሉ ከመመልከትም በላይ በጣም ከባድ ነው።" አሉኝ።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አዛን በሚሰማ ጊዜ ‹አልላሁመ ረበ ሀዚሂ አድደዕወቲ አትታመቲ ወስሰላቲል ቃኢመህ አቲ ሙሐመደኒል ወሲለተ ወልፈዲለተ ወብዐሥሁ መቃመን መሕሙደኒለዚ ወዐድተህ› ያለ ሰው የትንሳኤ ቀን ምልጃዬ ትፀድቅለታለች።" ትርጉሙም "የዚህ የተሟላ ጥሪና የምትቆመው ሶላት ጌታ የሆንከው አላህ ሆይ! ለሙሐመድ ወሲላና ፈዲላን ስጣቸው፤ ቃል የገባህላቸውን ምስጉን ስፍራም ስጣቸው።" ማለት ነው።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
"ድሃ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም: "እኛ ዘንድ ድሃ ማለት ዲርሀምና መጠቃቀሚያ እቃ የሌለው ሰው ነው።" አሉ። እርሳቸውም: "በኡመቴ ውስጥ ድሃ ማለት የትንሳኤ ቀን ሶላት፣ ፆም፣ ዘካ ይዞ የሚመጣ ነው። ነገር ግን ሲመጣ ይህንን ሰድቧል፣ ይህንን በዝሙት ዘልፏል፣ የዚህን ገንዘብ በልቷል፣ የዚህን ደም አፍስሷል፣ ይህንን መትቷል። ለዚህኛውም (ለተበዳዩ) ከመልካም ስራው ይሰጠዋል። ለዚያኛውም ከመልካም ስራው ይሰጠዋል። በርሱ ላይ ያለበት ሀቅ ተፈርዶ ሳይጠናቀቅ መልካም ስራው ካለቀ ደሞ ከነርሱ ወንጀል እየተወሰደ በርሱ ላይ ይጫንበትና ከዚያም እሳት ውስጥ ይጣላል።" አሉ።
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"የሐውዴ (የምንጬ ስፋቱ) አንድ ወር ያስኬዳል ፤ ውኃው ከወተት የነጣ፣ ሽታው ከሚስክ እጅግ የሚያውድ፣ የብርጭቆዎቹ ብዛት የሰማያት ኮኮቦች ያህል ናቸው። ከሷ አንዴ የጠጣ ከቶም መቼም አይጠማም።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የዚህ ሃይማኖት ጉዳይ ቀንና ምሽት የደረሰበት ስፍራ ሁሉ ይደርሳል። አላህ፤ በሀያሉ ሀይልም ይሁን በውርደታሞች ውርደት ይህንን ሃይማኖት እያንዳንዱ የግንብ (የከተማ) ቤት ውስጥም ይሁን የሳር ቤት (የገጠር ቤት) ውስጥ ሳያስገባው አይቀርም። ወይ አላህ በርሱ ኢስላምን የበላይ በሚያደርግበት ሀይል አልያም አላህ በርሱ ክህደትን በሚያዋርድበት ውርደት (ኢስላም የበላይነቱን ይጎናፀፋል)።"» ተሚም አድዳሪም እንዲህ ይል ነበር "ይህንንም በወገኖቼ አወቅኩት። ከወገኖቼ የሰለሙት መልካምን፣ ልቅናና ክብርን አገኙ። ከወገኖቼ መካከል የካዱትንም ውርደት፣ የበታችነትና ግብር አገኛቸው።"
ሶሒሕ ነው። አሕመድ ዘግበውታል።