Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 47 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"አንድም ነቢይ ለህዝቦቹ ያልተናገረውን ስለደጃል አንድ ነገር አልነግራችሁምን? እርሱ እውር ነው፣ እርሱ ጀነትና እሳት በሚመስል ነገር ከራሱ ጋር ይዞ ይመጣል። እርሷ ጀነት ናት የሚላት እሳት ናት። እኔ ኑሕም ህዝቦቹን እንዳስጠነቀቀው አስጠነቅቃችኋለሁ።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ። በናንተ ውስጥ የመርየም ልጅ ፍትሃዊ ዳኛ በቅርቡ ሆኖ ይወርዳል። መስቀልን ይሰባብራል፣ አሳማን ይገድላል፣ ግብርን ያነሳል፣ አንድም ሰው እስከማይቀበለው ድረስም ገንዘብ (ሀብት) ይበዛል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የትንሳኤ ቀን የትኛውም ባሪያ እድሜውን በምን እንዳጠፋው፣ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘውና ምን ላይ እንዳዋለው፣ በአካሉ ምን እንዳደረገበት ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም።'"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ ዘግበውታል።
"ሙስሊም ቀብር ውስጥ በተጠየቀ ጊዜ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ይመሰክራል።" ይህም አላህ እንዲህ እንዳለው ነው: {አላህ እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቱም ህይወት በመጨረሻይቱም (በመቃብር) በተረጋገጠው ቃል ላይ ያረጋቸዋል።} [ኢብራሂም:27]
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
'አላህ ምድርን በጭብጡ ያደርጋል፤ ሰማያትንም በቀኝ እጁ ይጠቀልልና ከዚያም ‹እኔ ነኝ ንጉሱ! የምድር ነገስታት የት አሉ?!› ይላል።'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ዘመኑ እስኪጣበብ ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም። አመቱ እንደ ወር ይሆናል፤ ወሩ እንደ ሳምንት ይሆናል፤ ሳምንቱም እንደ ቀን ይሆናል፤ ቀኑም እንደ ሰአት ይሆናል፣ ሰአቱም የተምር ዛፍ (ዘንባባ) ቅጠል እንደሚቃጠልበት ጊዜ (ያጠረ) ይሆናል።"
ሶሒሕ ነው። አሕመድ ዘግበውታል።
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አንድ ነገር ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ይህ የሚከሰተውም ዕውቀት ሊጠፋ የቀረበ ጊዜ ነው።" እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ ቁርኣን እየቀራን ፣ ልጆቻችንን እያቀራን፣ ልጆቻችንም ልጆቻቸውን እስከ እለተ ትንሳኤ እያቀሩ እንዴት ዕውቀት ይጠፋል?" አልኳቸው። እሳቸውም "እናትህ ትጣህ! ዚያድ በመዲና ጥልቅ ግንዛቤ ያለህ አድርጌ አይህ ነበርኩ። እነዚህ አይሁድና ክርስቲያን ተውራትና ኢንጂልን እየቀሩ ውስጣቸው ያለውን ምንም የማይሠሩ አይደሉምን?!" አሉኝ።
በሌላ ሰነድ ታግዞ ሶሒሕ ነው። ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።
"አዛን ባዩን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አምሳያ በሉ። ከዚያም በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ። እነሆ በኔ ላይ አንዲትን ሶላት ያወረደ በርሱ ምክንያት አላህ በርሱ ላይ አስር ሶለዋት ያወርድለታል። ከዚያም ለኔ ከአላህ ወሲላን ጠይቁልኝ። እርሷም ጀነት ውስጥ ያለች ደረጃ ናት። ከአላህ ባሮች መካከል ለአንድ ባሪያ እንጂ ለሌላ አትገባም። እርሱም እኔ እሆናለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ወሲላን ለኔ የጠየቀልኝ ሰው ለርሱ ምልጃዬ ትፀናለታለች።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።