Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 36 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ሰዎች የትንሳኤ ቀን ባዶ እግራቸውን፣ ራቁትና ያልተገረዙ ሆነው ይሰበሰባሉ።" እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ወንዶችም ሴቶችም ባጠቃላይ ከፊሉ ወደ ከፊሉ እየተመለከተ?" አልኳቸው። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "ዓኢሻህ ሆይ! ጉዳዩኮ ከፊሉ ወደ ከፊሉ ከመመልከትም በላይ በጣም ከባድ ነው።" አሉኝ።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ድሃ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም: "እኛ ዘንድ ድሃ ማለት ዲርሀምና መጠቃቀሚያ እቃ የሌለው ሰው ነው።" አሉ። እርሳቸውም: "በኡመቴ ውስጥ ድሃ ማለት የትንሳኤ ቀን ሶላት፣ ፆም፣ ዘካ ይዞ የሚመጣ ነው። ነገር ግን ሲመጣ ይህንን ሰድቧል፣ ይህንን በዝሙት ዘልፏል፣ የዚህን ገንዘብ በልቷል፣ የዚህን ደም አፍስሷል፣ ይህንን መትቷል። ለዚህኛውም (ለተበዳዩ) ከመልካም ስራው ይሰጠዋል። ለዚያኛውም ከመልካም ስራው ይሰጠዋል። በርሱ ላይ ያለበት ሀቅ ተፈርዶ ሳይጠናቀቅ መልካም ስራው ካለቀ ደሞ ከነርሱ ወንጀል እየተወሰደ በርሱ ላይ ይጫንበትና ከዚያም እሳት ውስጥ ይጣላል።" አሉ።
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"የሐውዴ (የምንጬ ስፋቱ) አንድ ወር ያስኬዳል ፤ ውኃው ከወተት የነጣ፣ ሽታው ከሚስክ እጅግ የሚያውድ፣ የብርጭቆዎቹ ብዛት የሰማያት ኮኮቦች ያህል ናቸው። ከሷ አንዴ የጠጣ ከቶም መቼም አይጠማም።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ፤ ብቸኛና አጋርም እንደሌለው፤ ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛው መሆናቸውን፤ ዒሳም የአላህ ባሪያና መልክተኛው፣ ወደመርየምም ያስተላለፈው ቃሉና ከርሱ የሆነ መንፈስ መሆኑን፣ ጀነትም እውነት መሆኗን፣ እሳትም እውነት መሆኗን የመሰከረ ሰው በማንኛውም ስራ ላይ ሆኖም አላህ ጀነት ያስገባዋል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።