Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 5 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ጀነት ውስጥ መቶ ደረጃዎች አሉ። በየሁሉም ደረጃዎች መካከል በሰማይና በምድር መካከል ያለውን ርቀት ያህል አለ። ፊርደውስ የላይኛው ደረጃ ነው። የጀነት ወንዞች የሚመነጩትም ከርሷ ነው። ከላዩዋ ያለውም (ጣሪያዋ) ዐርሽ ነው። አላህን በጠየቃችሁ ጊዜ ፊርደውስን ጠይቁት።"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ ዘግበውታል።
"ለተቸገረ (ባለዕዳ) ጊዜ የሰጠ ወይም ይቅር ያለ አላህ ከጥላው በስተቀር ጥላ በሌለበት የትንሳኤ ቀን ከዐርሹ ጥላ ስር ያስጠልለዋል።"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"አዋጅ! ከእኔ የሆነ ሐዲሥ በአልጋው ላይ ወደተደገፈ አንድ ሰውዬ ይደርሰውና፡ "በእኛና በእናንተ መካከል (የሚዳኘን) የአላህ መጽሐፍ ነው። በውስጡ የተፈቀደ ሆኖ ያገኘነውን (ብቻ) እንደ ሐላል እንቆጥረዋለን በውስጡም ሐራም ሆኖ ያገኘነውን (ብቻ) እንደ ሐራም እንቆጥረዋለን።" የሚልበት ወቅት ቅርብ ነው። በእርግጥ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሐራም (እርም) ያደረጉት ማንኛውም ነገር አላህ ሐራም እንዳደረገው ነው።'”
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።
"የትንሳኤ ቀን አላህ ከፍጡራኖች ከኔ ተከታዮች መካከል አንድ ሰው ይመርጣል። በሱ ላይም ዘጠና ዘጠኝ መዝገብ ይዘረጋበታል፤ ሁሉም መዝገብ ዓይን የሚያየውን ርቀት አምሳያ ያካልላል። ከዚያም "ከዚህ ውስጥ አንዳችም ቢሆን (አልሰራሁትም ብለህ) የምታስተባብለው አለን? ስራን ጠባቂ ጸሐፊዎቼ በድለውሀልን? " ብሎ ይጠይቀዋል። "ጌታዬ ሆይ በፍፁም!" ይላል። "ተቀባይነት ያለው ምክንያትስ \ ማስተባብያስ አለህን?" ይለዋል። " ጌታዬ ሆይ በፍፁም!" ይላል። አላህም "እንዴታ! እኛ ዘንድ አንድ መልካም ሥራ አለችህ። እነሆ ዛሬ ባንተ ላይ ምንም በደል የለም።" ይለዋል። ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ (ላኢላሀ ኢለ'ላህ ሙሐመዱ ረሱሉላህ) የሚልን ጽሑፍ የያዘች አንድ ካርድ ትወጣለች። አላህ "ሚዛንህ ላይ ተገኝ!" ይለዋል። እሱም "ጌታዬ ሆይ ይህቺ ካርድ ከነዚህ ሁሉ መዝገቦች ጋር (ስትነፃፀር) ምን ዋጋ አላት? " ይላል። አላህም "አንተ አትበደልም።" ይለዋል። መዝገቦቹ በአንድ በኩል ካርዷ በአንድ በኩል ለሚዛን ሲቀመጡ ካርዷ መዝገቦቹን ጠቅልላ ሚዛን ደፋች። ከአላህ ስም ጋር ምንም ሚዛን ሊደፋ አይችልም።
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።
"የትንሳኤ ቀን የትኛውም ባሪያ እድሜውን በምን እንዳጠፋው፣ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘውና ምን ላይ እንዳዋለው፣ በአካሉ ምን እንዳደረገበት ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም።'"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ ዘግበውታል።