Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 4 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ቀን በመካከላችን ቆሙና በርሷ ምክንያት ልቦናዎች የራዱበት፣ ዓይኖች ያነቡበትን ጥግ የደረሰን ምክር መከሩን። 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! የመከሩን ምክር የተሰናባች ምክር ሆኖብናልና ለእኛ የሚሰጡን አደራ አለን?' ተባሉ። እርሳቸውም ' አላህን በመፍራት፤ የሐበሻ ባሪያ እንኳ ቢሆን (መሪያችሁን) እንድትሰሙና እንድትታዘዙ አደራ እላችኋለሁ። ከኔ በኋላ ከባድ ልዩነትን ታያላችሁ፤ ስለሆነም በኔ ሱናና የተመሩ ቅን በሆኑት ምትኮቼ ሱና አደራችሁን! እርሷን በማኘኪያ ጥርሳችሁ ነክሳችሁ ያዙ! አደራችሁን አዳዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ! ሁሉም ቢድዓ (አዲስ መጤ) ጥመት ነውና።' አሏቸው።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"ሰዎች ግፈኛን ተመልክተው እጁን ካልያዙት አላህ ከርሱ በሆነ ቅጣት ሊያጠቃልላቸው ይቀርባል።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳወድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"አላህን በመፍራት፤ ባሪያ እንኳ ቢሾምባችሁ እንድትሰሙና እንድትታዘዙ አደራ እላችኋለሁ። እነሆ! ከናንተ መካከል ከኔ በኋላ የሚኖር ሰው ብዙ ልዩነትን ማየቱ አይቀርም፤ ስለሆነም በኔ ሱናና የተመሩ ቅን በሆኑት ምትኮቼ ሱና አደራችሁን! እርሷን በማኘኪያ ጥርሳችሁ ነክሳችሁ ያዙ! አደራችሁን አዳዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ! ሁሉም ቢድዓ (አዲስ መጤ) ጥመት ነውና።" አሏቸው።»
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።
«ጉዞ ላይ ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ነበርን። እርሳቸው ለመፀዳዳት ሄዱ። እኛም ትንሽዬን ወፍ ከነሁለት ጫጩቶቿ ተመለከትንና ጫጩቶቿን ወሰድን። ወፏም ክንፏን እያራገበች በራ መጣች። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: "ይህቺን ወፍ ልጆቿን ወስዶ ያስደነገጣት ማነው? ልጆቿን መልሱላት።" ጉንዳኖች ወረውት በእሳት ያቃጠልነውን ስፍራም ተመልክተው እንዲህ አሉ: "ይህንንስ ያቃጠለው ማነው?" እኛም "እኛ ነን።" አልን። እርሳቸውም: " እነሆ የእሳት ጌታ ካልሆነ በቀር ማንም በእሳት መቅጣት አይገባውም።" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ ዘግበውታል።