Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 20 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "አላህ እንዲህ አለ: የአደም ልጅ አስተባበለኝ ይህ ለርሱ አይገባም ነበር! ሰደበኝም ይህም ለርሱ አይገባም ነበር! እኔን ማስተባበሉማ ‹መጀመሪያ እንደፈጠረኝ (የትንሳኤ ቀን) አይመልሰኝም› ማለቱ ነው። በኔ ላይ እርሱን (የትንሳኤ ቀን) ከመመለስ ይልቅ መጀመሪያ መፍጠሩ ቀላል አይደለምን?። እኔን መስደቡማ ‹አላህ ልጅን ያዘ!› ማለቱ ነው። እኔ አንድ ነኝ፣ የሁሉ መጠጊያም ነኝ፣ አልወልድም፣ አልወለድም፣ ለኔም አንድም ቢጤ የለኝም።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
" አንድ ባሪያ የአንድን ባሪያ ነውር በዱንያ አይሸፍንም፤ የትንሳኤ ቀን አላህ ነውሩን የሚሸፍንለት ቢሆን እንጂ።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል "አላህ እንዲህ አለ: እኔ ባሪያዬ ባሰበኝ በኩል ነኝ። ባስታወሰኝም ጊዜ እኔ ከርሱ ጋር ነኝ። ለብቻው ካወሳኝ ለብቻዬ አወሳዋለሁ፤ በህብረት ካወሳኝ ደሞ ከርሱ የተሻለ በሆኑ ህብረቶች ዘንድ አወሳዋለሁ። አንድ ስንዝር ወደኔ ከቀረበ አንድ ክንድ ወደርሱ እቀርባለሁ። አንድ ክንድ ወደኔ ከቀረበ እጅ ሙሉ ወደርሱ እቀርባለሁ። እየተራመደ ወደኔ ከመጣ በሶምሶማ ወደርሱ እመጣለሁ።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የላቀውና ከፍ ያለው ጌታችን በሁሉም ሌሊት የመጨረሻ ሲሶ ሲቀር ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል። እንዲህም ይላል 'ማን ነው የሚለምነኝ የምመልስለት? ማን ነው የሚጠይቀኝ ለርሱ የምሰጠው? ማን ነው ምህረትን ከኔ የሚፈልገው ለርሱ የምምረው?'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።