Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 16 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
‹አላህ ይቀናል። አማኝ የሆነ ሰውም ይቀናል። የአላህ መቅናት ሰውዬው አላህ በሱ ላይ ክልክል ያደረገበትን ሲዳፈር ነው።›"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
የተወሰኑ የነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ባልደረቦች ወደነቢዩ በመምጣት እንዲህ ብለው ጠየቋቸው፦ " አንዳችን ለመናገር እጅግ የሚከብደንን ነገር ነፍሳችን ውስጥ እናገኘዋለን (በውስጣችን ይሰማናል)" እሳቸውም፦ "ይህን (በነፍሳችሁ ውስጥ) አገኛችሁን?" አሏቸው። እነሱም፦ "አዎን" አሉ። "ይህ ግልፅ ኢማን ነው።" በማለት መለሱላቸው።
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሰይጣን አንዳችሁ ዘንድ በመምጣት "ይህን የፈጠረው ማነው? ይህንንስ የፈጠረው?" እያለ ይጠይቃችኋል "ጌታህንስ የፈጠረው ማነው?" ብሎ እስኪጠይቃችሁ ድረስ ይደርሳል፤ ይህ ጥያቄ የደረሰው ጊዜ በአላህ ይጠበቅም ይከልከልም።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስፍራ መስጂዶች ናቸው። አላህ ዘንድ እጅግ የሚጠላው ስፍራ ገበያዎች ናቸው።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሚዛናዊ ሁኑ፤ በተቻለ መጠን ወደ እሱ ቅርብ ለመሆን ሞክሩ ከናንተ መካከል አንድም ሰው በስራው እንደማይድንም እወቁ!" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርሶም ቢሆኑ በስራዎት አይድኑምን?" አሉ። እርሳቸውም "አላህ ከርሱ በሆነ እዝነትና ችሮታ ካልሸፈነኝ በቀር እኔም ብሆን በስራዬ አልድንም።" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡ ' እኔ በሽርክና ከመጋራት ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃሁ ነኝ። ከኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እሱንም ማጋራቱንም እተወዋለሁ።'"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህ ወደ ቅርፃችሁና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ስራዎቻችሁ ይመለከታል።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህ ለናንተ ሶስት ነገር ይወድላችኋል፤ ሶስት ነገርንም ይጠላባችኋል። እርሱን መገዛታችሁን፣ በርሱ ላይ አንዳችንም አለማጋራታችሁን፣ ሁላችሁም በአላህ ገመድ መተሳሰራችሁንና አለመለያየታችሁን ለናንተ ይወድላችኋል። አሉባልታን፣ ጥያቄ ማብዛትንና ገንዘብ ማባከንን በናንተ ላይ ይጠላባችኋል።"»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።