Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 4 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
«የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ብሏል: ‹የአደም ልጅ ሆይ አንተ እስከለመንከኝና እስከከጀልከኝ ድረስ አንተ ላይ ካለብህ ወንጀልህ ጋርም እምርሃለሁ። (በመማሬም) ምንም አይመስለኝም፤ የአደም ልጅ ሆይ! ወንጀሎችህ የሰማይ ደመና ቢደርሱና ከዚያም ምህረት ብትጠይቀኝ እምርሃለሁ። (በመማሬም) ምንም አይመስለኝም፤ የአደም ልጅ ሆይ! ምድርን ሊሞላ በቀረበ ወንጀል እኔ ጋር ብትመጣ ከዚያም በኔ አንድንም ሳታጋራብኝ ብትገናኘኝ እኔም ምድርን ሊሞላ በቀረበ ምህረት ወዳንተ እመጣለሁ።›"»
ሐሰን ነው። ቲርሚዚ ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ ሑነይን የወጡ ጊዜ 'ዛቱ አንዋጥ' በምትባል የአጋርያን ዛፍ በኩል አለፉ። በርሷ ላይ (በረከትን በመፈለግ) መሳሪያዎቻቸውን ያንጠለጥሉባት ነበር። ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለነርሱ ‹ዛቱ አንዋጥ› እንዳላቸው ለኛም (የምናንጠለጥልበት) ‹ዛቱ አንዋጥ› አድርግልን።' አሉ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ 'ለአላህ ጥራት ተገባው! ይህ (የተናገራቹት) የሙሳ ህዝቦች {ለእነርሱ አማልክት እንዳላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን።} [አል አዕራፍ: 138] ብለው እንደተናገሩት ነው። ያ ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታዬ እምላለሁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች መንገድ ትከተላላችሁ።'"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"አንተ ልጅ ሆይ! እኔ ቃላቶችን አስተምርሃለሁ! የአላህን (ትእዛዛት) ጠብቅ (አላህ) ይጠብቅሀል፤ የአላህን (ትእዛዛት) ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ፤ የጠየቅክ ጊዜ አላህን ጠይቅ! ፤ እገዛን የፈለግክ ጊዜም በአላህ ታገዝ! እወቅ! ህዝብ ባጠቃላይ በአንዳች ነገር ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ እንኳ አላህ ለአንተ በፃፈልህ ነገር ካልሆነ በስተቀር አይጠቅሙህም። በአንዳች ነገር ሊጎዱህ ቢሰባሰቡም አላህ ለአንተ የፃፈብህ ካልሆነ በስተቀር አይጎዱህም። ብእሮቹም ተነስተዋል ፅሁፉም ደርቋል።"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚይና ሌሎችም ዘግበውታል