Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 4 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ ሑነይን የወጡ ጊዜ 'ዛቱ አንዋጥ' በምትባል የአጋርያን ዛፍ በኩል አለፉ። በርሷ ላይ (በረከትን በመፈለግ) መሳሪያዎቻቸውን ያንጠለጥሉባት ነበር። ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለነርሱ ‹ዛቱ አንዋጥ› እንዳላቸው ለኛም (የምናንጠለጥልበት) ‹ዛቱ አንዋጥ› አድርግልን።' አሉ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ 'ለአላህ ጥራት ተገባው! ይህ (የተናገራቹት) የሙሳ ህዝቦች {ለእነርሱ አማልክት እንዳላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን።} [አል አዕራፍ: 138] ብለው እንደተናገሩት ነው። ያ ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታዬ እምላለሁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች መንገድ ትከተላላችሁ።'"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"አላህ ከሻ (ከፈለገ) እና እከሌ ከሻ (ከፈለገ)' አትበሉ። ይልቁንም 'አላህ ከሻ (ከፈለገ) ከዚያም እከሌ ከሻ (ከፈለገ)' በሉ።"
ከሁሉም ሰነዶቹ አንፃር ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ነሳኢ በኩብራ ውስጥ፣ አሕመድ ዘግበውታል።
"ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ ሆይ! በኢስላም ውስጥ ከርሶ ውጪ ስለርሱ አንድንም ሰው የማልጠይቀው የሆነን አንድን ንግግር ንገሩኝ አልኳቸው። እርሳቸውም 'በአላህ አምኛለሁ በል ከዚያም ቀጥ በል።' አሉኝ"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊምና አሕመድ ዘግበውታል።