Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 3 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኢብኑ ዐባስ በስሟ ጠርቶ ለነገረኝ እኔ ግን ስሟን ለራሳኋት አንዲት የአንሷር ሴት እንዲህ አሏት "ከኛ ጋር ሐጅ ከማድረግ የከለከለሽ ምንድን ነው?" እርሷም "እኛ ከሁለት ግመል በቀር ሌላ አልነበረንም። የልጇ አባትና ልጇ በአንዱ ግመል ላይ ሐጅ አደረጉበት፤ ውሃ የምናመላልስበትን አንድ ግመል ደግሞ ለኛ ተወልን።" አለች። እርሳቸውም "ረመዳን የመጣ ጊዜ ዑምራ አድርጊ። በረመዳን የሚደረግ ዑምራ ሐጅ ከማድረግ ጋር ይስተካከላል።" አሏት።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጂሀድን እጅግ በላጭ ስራ አድርገን ነው የምናስበውና እኛም (ሴቶች) ከሀዲያንን እንታገልን?" እርሳቸውም፦ "በፍፁም! ነገር ግን እጅግ በላጩን ጂሀድ (ታገሉ!) (እርሱም) ተቀባይነት ያለው ሐጅ ነው።" አሉ።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
"ግንኙነትና ፆታዊ ስሜትን የሚያነሳሱን ሳይፈፅምና ሳያምፅ ለአሏህ ሐጅ አድርጎ የተመለሰ ልክ እናቱ እንደወለደችው ቀን (ከወንጀል ንፁህ) ሆኖ ይመለሳል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።