Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 121 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ

ዘጋቢ

ሁሉንም ዘጋቢዎች አሳይ (54)
"ሰዎች በአዛንና በመጀመሪያ ሰልፍ ያለውን ምንዳ ቢያውቁና እርሱንም እጣ ካልተጣጣሉ በቀር የማያገኙት ቢሆን ኖሮ እጣ ይጣጣሉ ነበር። (ወደ መስጊድ) ማልዶ የመሄድን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ ለርሱ ይሽቀዳደሙ ነበር። የዒሻና ሱብሒን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳኹም ቢሆን ይመጡ ነበር።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለበጎ ተግባርና ስለወንጀል ጠየቅኳቸው። እርሳቸውም " በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውን የጠላኸው ነገር ነው።" አሉኝ።»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"መልካም ነገሮች ሁሉ ምፅዋት ናቸው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ከጃቢር ሐዲሥ ዘግበውታል፤ ሙስሊምም ከሑዘይፋ ሐዲሥ ዘግበውታል
"ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው። ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሐላል (የተፈቀደ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። በመካከላቸው አብዛኛው ሰዎች የማያውቃቸው አሻሚ ጉዳዮች አሉ። አሻሚ ጉዳዮችን የተጠነቀቀ ሰው ሃይማኖቱንና ክብሩን ጠብቋል። አሻሚ ጉዳዮች ላይ የወደቀም ሰው ሐራም ላይ ወድቋል። የዚህ ሰው አምሳያ ልክ የተከለከለ ክልል ወሰን ዙሪያ እንደሚጠብቅና እንስሳዎቹም ወሰን አልፈው የተከለከለው ክልል ውስጥ ሊገቡ እንደቀረቡበት እረኛ ነው። አዋጅ! ለሁሉም ንጉስ ወሰን (ድንበር) አለው። አዋጅ! የአላህ ወሰን (ድንበር) ደግሞ ክልከላው ነው። አዋጅ! ሰውነት ውስጥ የምትገኝ ቁራጭ ስጋ አለች። እሷ ከተስተካከለች ሁሉም ሰውነት ይስተካከላል። እሷ ከተበላሸች ደግሞ ሁሉም ሰውነት ይበላሻል። አዋጅ! እሷም ልብ ናት።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስራ ምን እንደሆነ ጠየቅኳቸው። እሳቸውም 'ሶላትን በወቅቱ መስገድ።' አሉ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'ቀጥሎ ለወላጆች መልካም መዋል ነው።' አሉኝ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'በአላህ መንገድ መታገል ነው።' አሉ። እነዚህን ነገሩኝ። ጥያቄዬን ብጨምር እርሳቸውም ይጨምሩልኝ ነበር።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
'አዛን ባዩ: 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) ያለ ጊዜ አንዳችሁ ከልቡ 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' ካለ፤ ከዚያም አዛን ባዩ: 'አሽሀዱ አንላ ኢላሃ ኢለሏህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ እመሰክራለሁ።) ያለ ጊዜም 'አሽሀዱ አንላ ኢላሃ ኢለሏህ' ካለ፤ ከዚያም አዛን ባዩ: 'አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ' (ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ።) ያለ ጊዜም 'አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ' ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'ሐይየ ዐለስ-ሶላህ' (ኑ ወደ ሶላት) ባለ ጊዜም 'ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ' (ብልሀትም ሆነ ኃይል በአላህ ካልሆነ በቀር የለም።) ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'ሐይየ ዐለል ፈላሕ' (ኑ ወደ ስኬት!) ባለ ጊዜም 'ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ' (ብልሃትም ሆነ ኃይል በአላህ ካልሆነ በቀር የለም።) ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) ያለ ጊዜም 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'ላ ኢላሀ ኢለሏህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም።) ያለ ጊዜም 'ላ ኢላሀ ኢለሏህ' ካለ ጀነት ገባ።
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንድ ሙስሊም ‐ወይም ሙእሚን‐ የአላህ ባሪያ ውዱእ በሚያደርግበት ጊዜ ፊቱን ሲያጥብ በዓይኑ የተመለከተው ኃጢአት ሁሉ ከፊቱ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል። - እጁን ሲታጠብም እንዲሁ እጆቹ እየዳሰሰች የፈፀመችው ኃጢአት ሁሉ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል። - እግሩን ሲታጠብም እንዲሁ እግሮቹ ስትራመድ የፈፀመችው ሀጢአት ሁሉ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል። - ልክ እንደዚሁ እያለ ከኃጢአት ንጹሕ ሆኖ ከዉዱኡ እስኪወጣ ድረስ ከኃጢአቱ ይፀዳል።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።