Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 78 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው። አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ እጁን ወደ ዉዱእ እቃ ውስጥ ከመክተቱ በፊት እጁን ይጠብ! አንዳችሁ እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና።" የሙስሊም ዘገባ ላይ ደግሞ "አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ እጁን ሶስት ጊዜ ከማጠቡ በፊት ወደ እቃ ውስጥ አይንከረው! እርሱ እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለጌ (ጸያፍ) አልነበሩም፣ ጸያፍ ቃላትም አይናገሩም። እንዲህም ይሉ ነበር: ' ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ለአንድ ቀን በአላህ መንገድ ኬላ መጠበቅ ከዱንያና ውስጧ ካለው ይበልጣል፤ አንዳችሁ ጀነት ውስጥ ያለው አለንጋ የሚያህል ቦታ ከዱንያና ውስጧ ካለው ይበልጣል፤ ባሪያው በአላህ መንገድ ማልዶ መጓዙ ወይም አርፍዶ መጓዙ ከዱንያና ውስጧ ካለው ይበልጣል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከላቀውና ከተከበረው ጌታቸው ባስተላለፉት (ሐዲሥ) እንዲህ አሉ "አንድ ባሪያ አንድን ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "አላህ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ! " የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ!" ከዚያም ደግሞ ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!" የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ!" ከዚያም አሁንም ደግሞ ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!" የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ! የፈለግከውን ስራ በርግጥ ላንተ ምሬሃለሁ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁል ጊዜም በምሽት ወቅት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ መዳፋቸውን ይሰበስቡና ከዚያም ትንፋሻቸውን እየነፉበት {ቁል ሁወ አላሁ አሐድ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢ ናስ}ን ይቀሩበት ነበር። ከዚያም ከሰውነታቸው የቻሉትን በመዳፋቸው ያብሳሉ። (ሲያብሱም) ጭንቅላታቸውን፣ ፊታቸውንና ከሰውነታቸው የፊትለፊቱን በቅድሚያ ያብሳሉ። ይህንንም ሶስት ጊዜ ይፈፅሙታል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
"ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ!" ሶሓቦችም: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ምን ናቸው?" ብለው ጠየቁ፥ ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በአግባቡ ካልሆነ በስተቀር መግደል፣ አራጣ መብላት፣ የየቲምን ገንዘብ መብላት፣ ጦርነት በተፋፋመ እለት ማፈግፈግ፣ ከዝሙት ዝንጉ የሆኑ ጥብቅ ምእመናትን በዝሙት መዝለፍ ናቸው።" አሉ።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ኋላ ዑፈይር የሚባለው አህያ ላይ ተፈናጥጬ ሳለው "ሙዓዝ ሆይ አላህ በባሮቹ ላይ ያለውን ሐቅ፤ ባሮችስ አላህ ዘንድ ያላቸውን ሐቅ ታውቃለህን? " አሉ። "አላህና መልክተኛው ይወቁ !" አልኩኝ። እሳቸውም "አላህ በባሮቹ ላይ ያለው ሐቅ ሊገዙትና በሱ ላይም አንዳችንም ላያጋሩ ሲሆን፤ ባሮች አላህ ዘንድ ያላቸው ሐቅ ደግሞ በሱ ላይ አንዳችንም ያላጋራን ላይቀጣ ነው።" አሉ። "የአላህ መልክተኛ ሆይ ሰዎችን ላበስራቸውን?" አልኳቸው። እሳቸውም "አታበስራቸው (በዚህ ስራ ላይ ብቻ) ይደገፋሉ (ይሳነፋሉ)። " አሉ።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።