Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 5 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ከናንተ መካከል ለጁሙዓ ሶላት የመጣ ሰው ይታጠብ።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«ከመዲና መንገዶች በአንዱ መንገድ ላይ እርሱ ጀናባ ላይ ሆኖ ሳለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሲያገኙት ከእይታቸው ተደብቆ በመሄድ ገላውን ታጠበ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ፈልገው አጡት። በሚመጣበት ወቅትም "አቡ ሁረይራ ሆይ! የት ነበርክ?" አሉት። እርሱም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔን ያገኙኝ ጀናባ ላይ ሆኜ ስለነበር ገላዬን ሳልታጠብ ከርሶ ጋር መቀማመጥን ጠላሁ።" አላቸው። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ሱብሓነላህ! ሙእሚን'ኮ ነጃሳ አይሆንም።" አሉት።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«የጁመዓ ቀን ልክ እንደ ጀናባ ትጥበት ከታጠበ በኃላ ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የግመል ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በሁለተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የከብት ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በሶስተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ ቀንዳም ሙክት ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በአራተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የዶሮ ቁርባን እንዳቀረበ ነው። በአምስተኛው ወቅት ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የእንቁላል ቁርባን እንዳቀረበ ነው። ኢማሙ ለኹጥባ የወጣ ጊዜ መላእክቶቹም ተግሳፁን ለመስማት ይገኛሉ።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"እያንዳንዱ ሙስሊም በየሰባት ቀኑ አንድ ጊዜ ገላውን መታጠብ አለበት። ሲታጠብም ጭንቅላቱንም ገላውንም መታጠብ አለበት።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መታጠቢያ ውሃ አቀረብኩኝና በልብስም ሸፈንኩላቸው። እርሳቸውም በእጃቸው ላይ አፈሰሱና ሁለት እጃቸውን አጠቡ። ቀጥለው በቀኝ እጃቸው ግራ እጃቸው ላይ እያፈሰሱ ብልታቸውን አጠቡ። በእጃቸውም መሬቱን መቱና ጠረጉት። ቀጥለውም አጠቡት። ተጉመጠመጡ፣ አፍንጫቸው ውስጥም ውሃ አስገቡና አወጡ፣ ፊታቸውንና ክንዳቸውንም አጠቡ። ቀጥለው ጭንቅላታቸው ላይ ውሃ አፈሰሱ፣ በሰውነታቸው ላይም ውሃ አንቧቡ። ቀጥለው ገላቸውን ከታጠቡበት ስፍራ ራቅ አሉና እግራቸውን አጠቡ። ልብስ አቀበልኳቸው እርሳቸው ግን አልፈለጉትም። የሰውነታቸውን ርጥበት በእጃቸው እያራገፉት ሄዱ።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።