Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 5 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"አንዳችሁ የተኛ ጊዜ በማጅራቱ ላይ ሸይጧን ሶስት ቋጠሮ ይቋጥራል። በየሁሉም ቋጠሮ ላይም ረጅም ሌሊት አለና ተኛ! እያለ ይመታል። ከነቃና አላህን ካወሳ አንዱ ቋጠሮ ይፈታል። ዉዱእ ካደረገ አንዱ ቋጠሮ ይፈታል። ከሰገደ ደግሞ አንዱ ቋጠሮ ይፈታል። ያኔ ንቁና ነፍሱ የተደሰተች ሆኖ ያነጋል። ያለበለዚያ ግን ነፍሱ የከበደችውና የሰነፈ ሆኖ ያነጋል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ ዉዱእ በሌለው ጊዜ ዉዱእ እስኪያደርግ ድረስ አላህ ሶላቱን አይቀበለውም።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው። አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ እጁን ወደ ዉዱእ እቃ ውስጥ ከመክተቱ በፊት እጁን ይጠብ! አንዳችሁ እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና።" የሙስሊም ዘገባ ላይ ደግሞ "አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ እጁን ሶስት ጊዜ ከማጠቡ በፊት ወደ እቃ ውስጥ አይንከረው! እርሱ እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ ሶስት ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ ያውጣ፤ ሸይጧን በአፍንጫው ውስጥ ያድራልና።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንድ ሙስሊም ‐ወይም ሙእሚን‐ የአላህ ባሪያ ውዱእ በሚያደርግበት ጊዜ ፊቱን ሲያጥብ በዓይኑ የተመለከተው ኃጢአት ሁሉ ከፊቱ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል። - እጁን ሲታጠብም እንዲሁ እጆቹ እየዳሰሰች የፈፀመችው ኃጢአት ሁሉ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል። - እግሩን ሲታጠብም እንዲሁ እግሮቹ ስትራመድ የፈፀመችው ሀጢአት ሁሉ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል። - ልክ እንደዚሁ እያለ ከኃጢአት ንጹሕ ሆኖ ከዉዱኡ እስኪወጣ ድረስ ከኃጢአቱ ይፀዳል።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።