Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 11 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"አንዳችሁ የተኛ ጊዜ በማጅራቱ ላይ ሸይጧን ሶስት ቋጠሮ ይቋጥራል። በየሁሉም ቋጠሮ ላይም ረጅም ሌሊት አለና ተኛ! እያለ ይመታል። ከነቃና አላህን ካወሳ አንዱ ቋጠሮ ይፈታል። ዉዱእ ካደረገ አንዱ ቋጠሮ ይፈታል። ከሰገደ ደግሞ አንዱ ቋጠሮ ይፈታል። ያኔ ንቁና ነፍሱ የተደሰተች ሆኖ ያነጋል። ያለበለዚያ ግን ነፍሱ የከበደችውና የሰነፈ ሆኖ ያነጋል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ ዉዱእ በሌለው ጊዜ ዉዱእ እስኪያደርግ ድረስ አላህ ሶላቱን አይቀበለውም።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁሉም ሶላት ወቅት ዉዱእ ያደርጉ ነበር። 'እናንተስ እንዴት ነበር የምታደርጉት?' አልኩኝ። አነስም 'ዉዱእ እስካላጠፋን ድረስ (የነበረን) ዉዱእ ይበቃን ነበር።' አለ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ አንድ ጊዜ ዉዱእ አደርገዋል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
"አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው። አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ እጁን ወደ ዉዱእ እቃ ውስጥ ከመክተቱ በፊት እጁን ይጠብ! አንዳችሁ እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና።" የሙስሊም ዘገባ ላይ ደግሞ "አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ እጁን ሶስት ጊዜ ከማጠቡ በፊት ወደ እቃ ውስጥ አይንከረው! እርሱ እጁ የት እንዳደረች አያውቅምና።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ ሶስት ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ ያውጣ፤ ሸይጧን በአፍንጫው ውስጥ ያድራልና።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ከመካ ወደ መዲና ተመለስን። ውሃ የሚገኝበት መንገድ ላይ የደረስን ጊዜ ሰዎች ዐስርን በወቅቱ ለመስገድ በመቻኮል ፈጥነው ዉዱእ አደረጉ። ወደነርሱም ተረከዞቻቸው ውሃ ያልነካው ግልፅ ሆኖ ደረስንባቸው። በዚህ ወቅትም የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ " ተረከዞቻቸውን የዉዱእ ውሃ የማያስነኩ ከእሳት ወዮላቸው! ዉዱእን አዳርሳችሁ አድርጉ!"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
በዑሥማን ነፃ የወጣ የሆነው ሑምራን እንዳስተላለፈው እሱ "ዑሥማንን የውዱእ እቃ እንዲያመጡላቸው ሲጣሩ አየ። (የውዱእ እቃ ሲቀርብላቸውም) ከእቃው ውሀ በእጆቻቸው ላይ አፈሰሱ። እያፈሰሱም ሶስት ጊዜ አጠቧቸው። ከዚያም ቀኝ እጃቸውን በውዱእ እቃ ውስጥ አስገብተው ውሀ ዘገኑና በዚያው ተጉመጠመጡ አፍንጫቸው ውስጥም ውሀውን አስገብተው ድጋሚ አስወጡ። ከዚያም ፊታቸውን ሶስት ጊዜ፣ ሁለት እጆቻቸውንም እስከ ክርኖቻቸው ሶስት ጊዜ አጠቡ። ከዚያም ጭንቅላታቸውን አበሱ። ከዚያም ሁለት እግሮቻቸውን ሶስት ጊዜ አጠቡ። ከዚያም እንዲህ አሉ 'ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዚህ መልኩ ውዱእ ሲያደርጉ ተመልክቻቸዋለሁ። ከዚያም 'እኔ እንዳደረጉት አይነት ዉዱእ አድርጎ ከዚያም ነፍሱን ምንም በሃሳብ ሳያደፈርስ ሁለት ረከዐ የሰገደ ሰው ያሳለፈው ወንጀሉ ተምሮለታል።' አሉ።'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።