Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 10 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"የሱረቱል ከህፍ መጀመሪያ አስር አንቀጾችን የሸመደደ ሰው ከደጃል ይጠበቃል።" በሌላ ዘገባ "ከሱረቱል ከህፍ መጨረሻ አስር አንቀጾች… "
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ከፍ ያለው አላህ እንዲህ አለ: 'ሶላትን በኔና በባሪያዬ መካከል ለሁለት ከፈልኩት። ለባሪያዬም የጠየቀው አለው። ባሪያዬ {الْحَمْدُ لِلهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ} (ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው፤ የዓለማት ጌታ ለሆነው።) ያለ ጊዜ አላህ 'ባሪያዬ አመሰገነኝ!' ይላል። ባሪያው {الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ} (እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ ለሆነው።) ያለ ጊዜ አላህ 'ባሪያዬ እኔን አወደሰ!' ይላል። ባሪያው {مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ} (የፍርዱ ቀን ባለቤት ለሆነው።) ያለ ጊዜ አላህም 'ባሪያዬ አላቀኝ!' ይላል። - እንዲሁም 'ባርያዬ ጉዳዩን ወደ እኔ አስጠጋ።' - ይላል። ባሪያው {إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ} (አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታ እንለምናለን።) ያለ ጊዜ አላህም 'ይህ በኔና በባሪያዬ መካከል ያለ ቃል ኪዳን ነው። ለባሪያዬም የጠየቀውን አለው።' ይላል። ባሪያው {اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ، صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلا الضَّالِّينَ} (ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፤ የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን በሉ።) ) ያለ ጊዜ አላህም 'ይህ ለባሪያዬ ነው። ለባሪያዬም የጠየቀው አለው።' ይላል።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«ጂብሪል ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ተቀምጦ ሳለ ከበላዩ ድምፅ ሰማና ራሱን ቀና አደረገ። እንዲህም አለ: "ይህ ዛሬ የተከፈተ የሰማይ በር ነው። ከዛሬ በቀርም ተከፍቶ አያውቅም።" ከተከፈተው በርም መልአክ ወረደ። ጂብሪልም እንዲህ አለ: "ይህ ወደ ምድር የወረደ መልአክ ነው። ከዛሬ በቀርም በጭራሽ ወርዶ አያውቅም" መልአኩም ሰላምታን አቀረበና እንዲህ አለ: "ከአንተ በፊት ማንም ያልተሰጠው በሆነ ለአንተ ብቻ በተሰጠህ ሁለት ብርሃኖች አበስርሃለሁ። (እነርሱም) የመጽሐፉ መክፈቻ (ፋቲሓ) እና የበቀራ ምዕራፍ መጨረሻዎቹ ናቸው። ከነርሱም አንድም ፊደል አታነብም የሚሰጥህ ቢሆን እንጂ።"»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ። ሰይጣን የበቀራህ ምእራፍ የሚቀራበት ቤትን ይሸሻል።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ውስጥ ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አልኳቸው። " እርሳቸውም በድጋሚ "አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" አሉኝ። "{አላህ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው።} [አልበቀራህ: 255]" (አያተል ኩርሲይ) አልኩኝ። እሳቸውም ደረቴን በመምታት "በአላህ እምላለሁ! እውቀት ያስደስትህ አቡ ሙንዚር!" አሉኝ።
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁል ጊዜም በምሽት ወቅት ወደ ፍራሻቸው የተጠጉ ጊዜ መዳፋቸውን ይሰበስቡና ከዚያም ትንፋሻቸውን እየነፉበት {ቁል ሁወ አላሁ አሐድ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅ}ን፣ {ቁል አዑዙ ቢረቢ ናስ}ን ይቀሩበት ነበር። ከዚያም ከሰውነታቸው የቻሉትን በመዳፋቸው ያብሳሉ። (ሲያብሱም) ጭንቅላታቸውን፣ ፊታቸውንና ከሰውነታቸው የፊትለፊቱን በቅድሚያ ያብሳሉ። ይህንንም ሶስት ጊዜ ይፈፅሙታል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
"ቁርአንን ቅሩ! እርሱ የትንሳኤ ቀን ለባለቤቶቹ አማላጅ ሆኖ ይመጣል። ሁለቱን አብሪ የሆኑ ምዕራፎች ሱረቱል በቀራንና አሉ ዒምራንን ቅሩ። እነርሱ የትንሳኤ ቀን ልክ ደመና ወይም ጥላ መስለው ወይም ተጠባብቀው ረድፍ የሰሩ የወፎች ሁለት መንጋ መስለው ይመጣሉ። ለባለቤቶቻቸውም ይሟገታሉ። የበቀራን ምዕራፍ ቅሩ! እርሷን መያዝ በረከት ነው። እርሷን መተው ደግሞ የሚያስቆጭ ነው። ደጋሚዎችም አይችሏትም።"»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"በምሽት ውስጥ የመጨረሻዎቹን የበቀራህ ምእራፍ ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው ይበቁታል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።