Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 158 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ

ዘጋቢ

ሁሉንም ዘጋቢዎች አሳይ (53)
"ለአቅመ አዳም በደረሰ ሰው ላይ ሁሉ የጁሙዓ ቀን መታጠብ፣ ጥርሱን ሊፍቅና ካገኘም ሽቶ መቀባቱ ግዴታ ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ ከኢማም በፊት ጭንቅላቱን ቀና ያደረገ ጊዜ አላህ ጭንቅላቱን የአህያ ጭንቅላት እንዳያደርገው ወይም አላህ የሰውነት ቅርፁን የአህያ የሰውነት ቅርፅ እንዳያደርግበት አይፈራምን?!"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ፀጉር የምትቀጥልን፣ የምታስቀጥልን፣ የምትነቅስንና የምታስነቅስን ረግመዋል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
'ሴት ልጅ ከርሷ ጋር ባሏ ወይም ዘመዷ ከሌሉ በቀር ሁለት ቀን የሚያስኬድ መንገድን አትጓዝ። ሁለት ቀናት ላይ መፆም የለም፤ ዒደል ፊጥርና አድሓ። ከሱብሒ በኋላ ፀሀይ እስክትወጣ ድረስ ሶላት የለም፤ ከዐስር በኋላም ፀሀይ እስክትገባ ድረስ ሶላት የለም። ወደ ሶስት መስጂዶች ካልሆነ በቀርም ጓዝን ሸክፎ አይኬድም: ወደ መስጂደል ሐራም፣ ወደ መስጂደል አቅሷና ወደዚህ መስጂዴ።'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ ዉዱእ በሌለው ጊዜ ዉዱእ እስኪያደርግ ድረስ አላህ ሶላቱን አይቀበለውም።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«ዓኢሻን እንዲህ በማለት ጠየቅኳት: "የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ፆምን ቀዷ እያወጣች ሶላትን ቀዷ የማታወጣው ለምንድን ነው?" እርሷም "አንቺ ሐሩሪያ ነሽን?" አለችኝ። እኔም "ሐሩሪያ አይደለሁም። እንዲሁ እየጠየቅኩ ነው።" አልኳት። እርሷም "ይህ ጉዳይ ያጋጥመን ነበር። ፆምን ቀዷ በማውጣት (በማካካስ) ስንታዘዝ ሶላትን ቀዷ በማውጣት ግን አንታዘዝም ነበር።" አለች።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ‐ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ‐ ከስለት ከለከሉ። እንዲህም አሉ "እርሱ መልካምን ይዞ አይመጣም። በስለት የሚገኘው ትርፍ ስስታም ተገዶ ማውጣቱ ብቻ ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"እናንተ የሴቶች ስብስቦች ሆይ! ምጽዋት ስጡ! እኔ አብዛኛው የእሳት ነዋሪዎች ሆናችሁ አይቻችኋለሁ።" ሴቶቹም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በምን ምክንያት?" አሉ። እርሳቸውም "እርግማን ታበዛላችሁ፤ አኗኗሪን ትክዳላችሁ። አይምሮና ዲናቸው የጎደለ ሆኖ፤ ቆራጥ የሆነን ወንድ ልጅ ልብ የሚወስድም እንደናንተ አልተመለከትኩም!" አሉ። ሴቶቹም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የዲናችንና አይምሯችን መጉደል ምንድን ነው?" አሉ። እርሳቸውም "የአንድ ሴት ልጅ ምስክር እንደ ግማሽ የወንድ ምስክር አይደለም የሚቆጠረው?" አሉ። ሴቶቹም "እንዴታ!" አሉ። እርሳቸውም "ይህም የአይምሮዋ መጉደሉ ነው። የወር አበባ ባየች ጊዜ አትሰግድምም አትጾምም አይደል?" አሉ። ሴቶቹም "እንዴታ!" አሉ። እርሳቸውም "ይህም የዲናቸው መጉደሉ ነው።" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።