Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 12 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"የሙእሚኖች እናት ሆይ! ስለአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር ንገሪኝ! እሷም 'ቁርአን አትቀራምን?' አለችኝ። እኔም 'እንዴታ!' አልኩኝ። እሷም ' የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ስነምግባር ቁርአን ነበር።' አለችኝ።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ረጅሙ የሐዲሥ ጥቅል ውስጥ ዘግበውታል።
«ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጫማ ሲለብሱ፣ ሲያበጥሩ፣ ሲፅዳዱና በሁሉም ጉዳያቸው ቀኝን መጠቀም ይወዱ ነበር።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ነገ ይህንን ባንዲራ አላህ በርሱ እጅ ድልን ለሚያጎናፅፍ፣ አላህና መልክተኛውን ለሚወድ፣ አላህና መልክተኛውም የሚወዱት ለሆነ ሰው እሰጠዋለሁ።" ሰዎችም ለማን ነው የሚሰጠው? በሚል ሌሊታቸውን ተጠምደውበት አደሩ። ሰዎችም ያነጉ ጊዜ ሁሉም ባንዲራው እንዲሰጠው ተስፋ በማድረግ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ ማልደው ሄዱ። እርሳቸውም "ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ የት አለ? አሉ። ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አይኑን አሞታል" ተባሉ። እርሳቸውም "ሰው ላኩበት!" አሏቸው። እርሱም ተይዞ መጣና የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዓይኑ ላይ ተፉና ዱዓ አደረጉለት። እርሱም ከዚህ በፊት ምንም በሽታ እንዳልነበረበት ሆኖ ተፈወሰ። ባንዲራውንም ሰጡት። ዐሊይም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እንደኛው አምሳያ እስኪሆኑ ድረስ ልዋጋቸውን?" በማለት ጠየቃቸው። እርሳቸውም አሉት: "ቀያቸው እስክትሰፍር ድረስ ተረጋግተህ ተጓዝ። ቀጥሎ ወደ እስልምና ጥራቸው። በነርሱ ላይ ግዴታ የሚሆንባቸውንም የአላህ ሐቅ ንገራቸው። በአላህ እምላለሁ! ለአንተ ቀይ ግመል ከሚኖርህ በአንተ ሰበብ አላህ አንድ ሰው ቢመራልህ የተሻለ ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰዎች ባጠቃላይ ይበልጥ ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ ሰው ነበሩ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።