Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 5 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
«የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - አንድ ኢብኑ ሉትቢየህ ተብሎ የሚጠራን ሰውዬ የበኒ ሱለይምን ጎሳ ዘካ እንዲሰበስብ ሾሙት፤ ሰብስቦ ሲመጣም ተሳሰቡት። እርሱም ሲያስረክብ እንዲህ አለ: "ይህ የናንተ ገንዘብ ነው። ይህ ደሞ የተሰጠኝ ስጦታ ነው።" የአላህም መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: "እውነት ላንተ የተሰጠ ስጦታ ከሆነ ስጦታው ቤትህ እስኪመጣ ድረስ እናት አባትህ ቤት አትቀመጥም ነበር?" ቀጥለውም ኹጥባ አደረጉልን: አላህን ካመሰገኑና ካወደሱ በኋላም እንዲህ አሉ: "ከዚህ በመቀጠል እኔ አላህ በሰጠኝ ሹመት መሰረት ከናንተ መካከል አንድን ሰው ከሾምኩት በኃላ እኔ ዘንድ በመምጣት ይህ የናንተ ገንዘብ ነው። ይህ ደግሞ የተሰጠኝ ስጦታ ነው ይላል እንዴ?! ስጦታው ቤቱ እስኪመጣለት ድረስ እናት አባቱ ቤት አይቀመጥም ነበር? በአላህ እምላለሁ! ከናንተ መካከል አንዱ ያለአግባብ አንዳችን አይወስድም የትንሳኤ ቀን ተሸክሞት አላህን ቢገናኝ እንጂ ከናንተ መካከል አላህ ፊት የምትጮህ ግመል ወይም የምታጋሳ ከብት ወይም የምትጮህ በግ ተሸክሞ የሚቀርብን ሰው አውቃለሁ።" ቀጥለው "አላህ ሆይ መልዕክቴን አድርሻለሁን?" እያሉ የብብታቸው ንጣት እስኪታይ ድረስ እጃቸውን ከፍ አደረጉ። ይህንን ሁሉ አይኔም አይቷል ጆሮዬም ሰምቷል።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሁላችሁም እረኞች (ሀላፊ) ናችሁ። ስለምትጠብቁት ነገርም ትጠየቃላችሁ። በሰዎች ላይ የተሾመ መሪ እረኛ (ሀላፊ) ነው። ስለነርሱም ይጠየቃል። ወንድ በቤተሰቡ ላይ እረኛ (ሀላፊ) ነው። ስለነርሱም ይጠየቃል። ሴት ልጅ በቧሏ ቤትና በልጆቹ ላይ እረኛ (ሀላፊ) ናት። ስለነርሱም ትጠየቃለች። ባሪያ በአለቃው ገንዘብ ላይ እረኛ (ሀላፊ) ነው። ስለርሱም ይጠየቃል። አዋጅ! ሁላችሁም እረኞች (ሀላፊ) ናችሁ። ስለምትጠብቁት ነገርም ትጠየቃላችሁ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር መሪያችንን በችግርም ጊዜ ሆነ በድሎት ፣ በንቃትም ጊዜ ሆነ በጠላንበትም ጊዜ ፣ በኛ ላይ አድሎ ቢደረግብንም እንኳ እንድንሰማውና እንድንታዘዘው፤ የስልጣን ባለቤትም በጉዳዩ ከአላህ ግልፅ ማስረጃ የመጣበትን ግልፅ ክህደት እስካላያችሁበት ድረስ (ስልጣኑን) ላንጋፋው፣ የትም ብንሆን እውነትን እንድንናገር ፣ በአላህ መንገድም የወቃሽን ወቀሳ ላንፈራ ቃል ተጋብተናል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህ አንድ ሀላፊነት ላይ ሹሞት የተሰጠውን ሀላፊነት የሚያታልል ሆኖ የሚሞት ባሪያ የለም አላህ በርሱ ላይ ጀነትን እርም የሚያደርግ ቢሆን እንጂ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ለወደፊት የምታወግዟቸው ጉዳዮችና አድልዎ ይከሰታል!' ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ያዙናል?' አሉ። እርሳቸውም 'በናንተ ላይ ያለባችሁን ግዴታ ትወጣላችሁ። ለናንተ ያላችሁን ሐቅ ደግሞ ከአላህ ትጠይቃላችሁ።' አሉ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።