Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 5 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ሰዎች ግፈኛን ተመልክተው እጁን ካልያዙት አላህ ከርሱ በሆነ ቅጣት ሊያጠቃልላቸው ይቀርባል።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳወድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"ከእናንተ መካከል መጥፎ ሢሠራ የተመለከተ፥በእጁ ይለውጠው (ያስተካክለው)፤ ይህንን ካልቻለ በምላሱ ይከላከል፤ ይህንንም ካልቻለ በቀልቡ (ልቡ) ይጥላ ይህ ግን ደካማው የኢማን ክፍል ነው።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ከናንተ መካከል እውነታን ተመልክቶ ወይም አውቆ ከመናገር ማናችሁንም ቢሆን ለሰዎች ያለው ፍራቻ እንዳይከለክለው።"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"በአላህ ድንበር ላይ በአግባቡ የቆሙና የርሱን ድንበር የሚተላለፉ ሰዎች ምሳሌ በመርከብ ላይ (ቦታ ለመምረጥ) እጣ እንደተጣጣሉ ሰዎች ምሳሌ ነው። (በእጣው መሰረት) ከፊሉን የመርከቡ የላይኛው ክፍል ሲደርሰው ከፊሉን ደግሞ የታችኛው ክፍል ደረሰው። የመርከቡ ታችኛው ክፍል ያሉት ውሃ ለመጠጣት የፈለጉ ጊዜ ላይኛው ክፍል ባሉት በኩል ያልፉ ነበርና "እኛም (ውሃ ለማግኘት) ፋንታችንን መርከቡን ብንሸነቁርና ከኛ በላይ ያሉትን ባናውካቸው መልካም ነው።" ተባባሉ። ከላይ ያሉት የታችኞቹ ፍላጎታቸውን እንዲፈፅሙ ከተዉዋቸው ሁሉም ይጠፋሉ። እጃቸውን ከያዙ ደግሞ እነሱም ይድናሉ። ሁሉም ይድናሉ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
"እነሆ የሚዋሹና ግፈኛ የሆኑ መሪዎች ይመጣሉ። ውሸታቸውን አምኖ የተቀበለና በበደላቸው ላይ ያገዛቸው እርሱም ከኔ አይደለም። እኔም ከርሱ አይደለሁም። ወደኔ ምንጭም (ወደ ሐውድ) አይመጣም። የነርሱን ውሸት አምኖ ያልተቀበለና በበደላቸውም ላይ ያላገዛቸው ሰው ደሞ እርሱ ከኔ ነው። እኔም ከርሱ ነኝ። ወደኔ ምንጭ (ሐውድም) ይመጣል።"
ሶሒሕ ነው። አሕመድ ዘግበውታል።