Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 25 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
«ጀነት ውስጥ (የጀነት ሰዎች) በየጁሙዓው የሚሄዱባት ሱቅ አለች። በስተሰሜን ንፋስ ትነፍስና ፊታቸውንና ልብሳቸውን ትገርፋለች። (በዚህም) ውበትና ቁንጅናን ይጨምራሉ። ውበትና ቁንጅናቸው ጨምሮም ወደ ሚስቶቻቸው ይመለሳሉ። ሚስቶቻቸውም እንዲህ ይሏቸዋል: "በአላህ እንምላለን! ከኛ ከተለያቹ በኋላ ውበትና ቁንጅናችሁ ጨምሯል።" እነርሱም ለሚስቶቻቸው "በአላህ እንምላለን! እናንተም ከኛ ከተለያችሁ በኋላ ውበትና ቁንጅና ጨምራችኋል።"»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአብዛኛው ሰዎችን ጀነት ስለሚያስገባው ነገር ተጠየቁ፤ እሳቸውም "አላህን መፍራት እና መልካም ስነምግባር ነው።" አሉ። በአብዛኛው ሰዎችን እሳት ስለሚያስገባቸው ነገርም ተጠየቁ። እሳቸውም "ምላስና ብልት ነው።" አሉ።
ሐሰኑን ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
'አሁን ላይ እኔ ያላየኋቸው ሁለት አይነት የእሳት ባለቤቶች አሉ። (እነሱም) ሰዎችን የሚደበድቡበት እንደከብት ጭራ የመሰለ አለንጋ ያላቸው ሰዎች እና ለብሰው የተራቆቱ የሆኑ ራሳቸው ተዘንብለው ሌሎችን ለክፉ የሚጋብዙ፤ ጭንቅላታቸው እንደተዘነበለ የግመል ሻኛ የሆነ ሴቶች ናቸው። እነዚህ ጀነት አይገቡም፤ መዓዛዋንም አያገኙም። የጀነት ሽታዋም (እነሱ ካሉበት) የሆነ ያክል ርቆ ይገኛል።'"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"በኔ ላይ ጀነትና እሳት ቀረቡ። እንደዛሬ መልካምና መጥፎ ነገር ተመልክቼ አላውቅም። እኔ የማውቀውን ብታውቁ ኖሮ ትንሽ ስቃቹ ብዙ ታለቅሱ ነበር።"» አነስ እንዲህ አለ: "በአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሶሓቦች ላይ ከዚህ ቀን የበለጠ ከባድ ቀን መጥቶ አያውቅም።" አነስ እንዲህም አለ: «ሶሓቦች ጭንቅላታቸውን ሸፍነው እየተንሰቀሰቁ አለቀሱ። ዑመርም ተነሳና እንዲህ አለ: "በአላህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ ነቢይነት ወደድን።" ያ ሰውዬም ተነሳና እንዲህ አለ: "አባቴ ማን ነው?" እርሳቸውም "አባትህ እገሌ ነው።" አሉት። በዚህም ጊዜ ይህቺ አንቀፅ ወረደች {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ ቢገለፁ ከሚያስከፏችሁ ነገሮች አትጠይቁ።} [አልማኢዳህ:101]»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ብሏል: "ደጋግ ለሆኑ ባሪያዎቼ ዓይን ያላየችው፤ ጆሮ ያልሰማችው፤ በሰው ቀልብ ላይ ውል ያላለን ፀጋ አዘጋጅቼላቸዋለሁ።"» «አቡ ሁረይራም እንዲህ አለ: "ከፈለጋችሁ ይህንን አንብቡ {ይሰሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለነርሱ የተደበቀላቸውን (ፀጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም።} [አስሰጅዳ:17]"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ሳለን ድንገት አስደንጋጭ ድምፅ ሰሙ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" አሉ። እኛም "አላህና መልክተኛው አዋቂዎች ናቸው።" አልን። እርሳቸውም " ይህ ከሰባ አመት ጀምሮ እሳት ውስጥ የተወረወረ ድንጋይ ነው። እርሱም እሳት ውስጥ ወደ ጥልቀቷ መጨረሻ ዛሬ እስኪደርስ ድረስ እየተምዘገዘገ ነበር።" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ጀነት ውስጥ ዛፍ አለች። ረጅም ጊዜ የተቀለበችና ፈጣን የሆነችን ፈረስ ምርጥ ጋላቢ መቶ አመት ጋልቦ ይህቺን ዛፍ አያቋርጣትም።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ፤ ብቸኛና አጋርም እንደሌለው፤ ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛው መሆናቸውን፤ ዒሳም የአላህ ባሪያና መልክተኛው፣ ወደመርየምም ያስተላለፈው ቃሉና ከርሱ የሆነ መንፈስ መሆኑን፣ ጀነትም እውነት መሆኗን፣ እሳትም እውነት መሆኗን የመሰከረ ሰው በማንኛውም ስራ ላይ ሆኖም አላህ ጀነት ያስገባዋል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።