Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 25 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ጀነት ወደ እያንዳንዳችሁ ከጫማው ማሰሪያ የበለጠ ቅርብ ናት። እሳትም እንደዚሁ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
"በሁለት መንገጭላዎቹ መካከል እና በሁለት እግሮቹ መካከል ያሉትን አካላት (ሊጠብቅ) ዋስትና ለገባልኝ እኔም ጀነትን ዋስትና እገባለታለሁ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
"ሞት በቡራቡሬ ሙክት ተመስሎ ተይዞ ይመጣል። ተጣሪም እንዲህ በማለት ይጣራል: "የጀነት ባለቤቶች ሆይ!" ተንጠራርተው ይመለከታሉ። "ይህንን ታውቁታላችሁን?" ይላቸዋል። "አዎን ይህ ሞት ነው ሁሉም ተመልክቶታል።" ይላሉ። ቀጥሎ ተጣሪው እንዲህ በማለት ይጣራል "የእሳት ባለቤቶች ሆይ!" ተንጠራርተው ይመለከታሉ። "ይህንን ታውቁታላችሁን?" ይላቸዋል። "አዎን ይህ ሞት ነው ሁሉም ተመልክቶታል።" ይላሉ። ይታረዳል ቀጥሎ እንዲህ ይላቸዋል "የጀነት ባለቤቶች ሆይ! (ከዚህ በኋላ) ዘላለማዊ ሕይወት እንጂ ሞት የለባችሁም። የእሳት ባለቤቶች ሆይ! (ከዚህ በኋላ) ዘላለማዊ ሕይወት እንጂ ሞት የለባችሁም።" ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ፦ {እነሱም (አሁን) በዝንጋቴ ላይ ሆነው ሳሉ ነገሩ በሚፈረድበት ጊዜ የቁጭቱን ቀን አስፈራራቸው።} [መርየም: 39] የሚለውን አንቀፅ አነበቡ። "እነዚህ በዱንያ ዝንጋቴ ውስጥ ናቸው።" {እነሱም የማያምኑ ናቸው።} [መርየም: 39]"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
«(ለጀነት ነዋሪዎች) አንድ ተጣሪ ይጣራና "ለናንተ ጤና አላችሁ መቼም አትታመሙም፤ ለናንተ ህይወት አላችሁ መቼም አትሞቱም፤ ለናንተ ወጣትነት አላችሁ መቼም አታረጁም፤ ለናንተ በፀጋ ውስጥ መጣቀም አላችሁ መቼም አትቸገሩም።" ይህም ይህ የአላህ ዐዘ ወጀል ንግግር ነው: {ይህች ጀነት ትሰሩት በነበራችሁት ተሰጣችኋት በማለት ይጠራሉ።} [አልአዕራፍ: 43]»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"በአሏህ ሳያጋራ አሏህን የተገናኘ ጀነት ገብቷል፤ እያጋራበት አሏህን የተገናኘ ደግሞ እሳት ገብቷል።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«ጀነት ውስጥ የአንዳችሁ ትንሹ ደረጃ አላህ ለርሱ "ተመኝ" ይለዋል። እርሱም ደጋግሞ ይመኛል። አላህም ለርሱ "ተመኘህን?" ይለዋል። እርሱም "አዎን" ይላል። አላህም ይለዋል: "ላንተ የተመኘኸውንም ከርሱም ጋር የርሱን አምሳያ ሌላም ይሰጥሃል።"»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«"አንተ አቡ ሰዒድ ሆይ! በአላህ ጌትነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ ነቢይነት የወደደ ሰው ለርሱ ጀነት ግድ ሆናለታለች።" አቡ ሰዒድም በዚህች ንግግር ተደሰተና እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በድጋሚ ይንገሩኝ!" እርሳቸውም ደገሙለትና አክለውም እንዲህ አሉ: "ሌላም አንድ ስራ አለች። አንድ ባሪያ በርሷ ሰበብ ጀነት ውስጥ መቶ ደረጃ ከፍ ይደረጋል። በየሁሉም ደረጃ መካከልም ያለው ርቀትም በሰማይና በምድር መካከል እንዳለው ርቀት ነው።" እርሱም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምንድናት እርሷ?" አለ። እርሳቸውም "በአላህ መንገድ መታገል! በአላህ መንገድ መታገል!" አሉት።»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
«የጀነት ሰዎች ጀነት የገቡ ጊዜ አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ይላል "አንዳች ነገር እንድጨምርላችሁ ትፈልጋላችሁን?" እነርሱም "ፊታችንን አላበራህልንምን? ጀነት አስገብተህስ ከእሳት አላዳንከንምን?" ይላሉ። ነቢዩ እንዲህ አሉ "የፊቱን ግርዶሽ ይገልጣል። ወደ ጌታቸው ዐዘ ወጀል ከመመልከት የበለጠ ተወዳጅ የሆነ አንዳችም ነገር አልተሰጣቸውም።"»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።