Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 4 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"እናንተ የሴቶች ስብስቦች ሆይ! ምጽዋት ስጡ! እኔ አብዛኛው የእሳት ነዋሪዎች ሆናችሁ አይቻችኋለሁ።" ሴቶቹም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በምን ምክንያት?" አሉ። እርሳቸውም "እርግማን ታበዛላችሁ፤ አኗኗሪን ትክዳላችሁ። አይምሮና ዲናቸው የጎደለ ሆኖ፤ ቆራጥ የሆነን ወንድ ልጅ ልብ የሚወስድም እንደናንተ አልተመለከትኩም!" አሉ። ሴቶቹም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የዲናችንና አይምሯችን መጉደል ምንድን ነው?" አሉ። እርሳቸውም "የአንድ ሴት ልጅ ምስክር እንደ ግማሽ የወንድ ምስክር አይደለም የሚቆጠረው?" አሉ። ሴቶቹም "እንዴታ!" አሉ። እርሳቸውም "ይህም የአይምሮዋ መጉደሉ ነው። የወር አበባ ባየች ጊዜ አትሰግድምም አትጾምም አይደል?" አሉ። ሴቶቹም "እንዴታ!" አሉ። እርሳቸውም "ይህም የዲናቸው መጉደሉ ነው።" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አላህ ተባረከ ወተዓላ ለጀነት ነዋሪዎች እንዲህ ይላቸዋል: 'እናንተ የጀነት ነዋሪዎች ሆይ!' እነርሱም 'ደጋግመን በደስተኝነት አቤት ብለናል' ይላሉ። አላህም 'ተደሰታችሁን?' ይላቸዋል። እነርሱም 'ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካል ያልሰጠኸውን ሰጥተኸን እንዴት ነው የማንደሰተው?' ይላሉ። እርሱም 'እኔ ከዚህም የተሻለ ነገር እሰጣችኋለሁ።' ይላል። እነርሱም 'ጌታችን ሆይ! ከዚህ የተሻለ ምን አይነት ነገር ይኖራል?' ይላሉ። አላህም 'በናንተ ላይ ውዴታዬን አሰፍናለሁ። በናንተ ላይ ከዚህ በኋላ መቼም አልቆጣም።' ይላቸዋል።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሞት በቡራቡሬ ሙክት ተመስሎ ተይዞ ይመጣል። ተጣሪም እንዲህ በማለት ይጣራል: "የጀነት ባለቤቶች ሆይ!" ተንጠራርተው ይመለከታሉ። "ይህንን ታውቁታላችሁን?" ይላቸዋል። "አዎን ይህ ሞት ነው ሁሉም ተመልክቶታል።" ይላሉ። ቀጥሎ ተጣሪው እንዲህ በማለት ይጣራል "የእሳት ባለቤቶች ሆይ!" ተንጠራርተው ይመለከታሉ። "ይህንን ታውቁታላችሁን?" ይላቸዋል። "አዎን ይህ ሞት ነው ሁሉም ተመልክቶታል።" ይላሉ። ይታረዳል ቀጥሎ እንዲህ ይላቸዋል "የጀነት ባለቤቶች ሆይ! (ከዚህ በኋላ) ዘላለማዊ ሕይወት እንጂ ሞት የለባችሁም። የእሳት ባለቤቶች ሆይ! (ከዚህ በኋላ) ዘላለማዊ ሕይወት እንጂ ሞት የለባችሁም።" ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ፦ {እነሱም (አሁን) በዝንጋቴ ላይ ሆነው ሳሉ ነገሩ በሚፈረድበት ጊዜ የቁጭቱን ቀን አስፈራራቸው።} [መርየም: 39] የሚለውን አንቀፅ አነበቡ። "እነዚህ በዱንያ ዝንጋቴ ውስጥ ናቸው።" {እነሱም የማያምኑ ናቸው።} [መርየም: 39]"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ጀነት ውስጥ ዛፍ አለች። ረጅም ጊዜ የተቀለበችና ፈጣን የሆነችን ፈረስ ምርጥ ጋላቢ መቶ አመት ጋልቦ ይህቺን ዛፍ አያቋርጣትም።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።