Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 7 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህቺን አንቀፅ አነበቡ {እርሱ ያ በአንተ ላይ መጽሀፉን ያወረደ ነው። ከእርሱ (ከመፅሀፉ) ግልጽ የሆኑ አንቀጾች አሉ። እነሱ የመጽሐፉ መሠረቶች ናቸው። ሌሎችም ተመሳሳዮች አሉ። እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች ማሳሳትን በመፈለግና ማጣመምን በመፈለግ ከርሱ የተመሳሰለውን ይከታተላሉ። (ትክክለኛ) ፍቺውንም አላህ ብቻ እንጂ ሌላ አያውቀውም። በዕውቀትም የጠለቁት "በርሱ አምነናል፤ ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው" ይላሉ። የአእምሮ ባለቤቶችም እንጅ (ሌላው) አይገሰጽም።} [ኣሉ ዒምራን: 7] ቀጥለው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፦ " እነዚያ ከቁርኣን የተመሳሰለውን የሚከተሉትን ከተመለከትሽ አላህ ተጠንቀቁዋቸው ብሎ የጠቀሳቸው እነሱ ናቸው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የሰው ልጅ እንደሆዱ መጥፎን ቋት አልሞላም። የአደም ልጅ ወገቡን ቀና የሚያደርጉለት ጥቂት ጉርሻዎች ይበቁታል። (መጥገቡ) የማይቀር ከሆነ (የሆዱን) ሲሶውን ለምግቡ፣ ሲሶውን ለመጠጡ፣ ሲሶውን ለትንፋሹ ያድርግ።"
ሶሒሕ ነው። ኢማም አሕመድ፣ ቲርሚዚይ፣ ነሳኢይ እና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል
"ዕውቀትን ዑለሞችን ልትፎካከሩበት (በሊቃውንት ፊት ለመታየት)፣ ቂሎችን ልትሟገቱበት፣ በመድረኮች ላይ ቅድሚያ እንድትመረጡበት በማለም እንዳትቀስሙ። ይህን የፈፀመ (ለርሱ) እሳት አለው እሳት አለው።"
ሶሒሕ ነው። ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።
"ሰሌን ላይ የሚተኛ ሰው ቆዳው ላይ ሰንበር እንደሚያወጣው ፈተናም በቀልብ ላይ በተደጋጋሚ ትቀርባለች። ፈተናዋ ወደ ውስጡ የገባችበት ማንኛውም ቀልብ ጥቁር ጠብታ ቀልቡ ላይ ታርፋለች። ፈተናዋን ያወገዘ ማንኛውም ቀልብ ደሞ ነጭ ጠብታ ቀልቡ ላይ ታርፋለች። ይህም ሁለት ቀልብ እስኪሆን ድረስ ነው። ሰማይና ምድር እስከዘወተሩ ድረስ ፈተና የማይጎዳት እንደ ለስላሳ ድንጋይ የነጣ ቀልብ እና ሌላኛው ደግሞ እንደተገለበጠ ኩባያ ከስሜቱ ጋር የተስማማውን ካልሆነ በቀር ጥሩን ጥሩ የማይል መጥፎንም የማያወግዝ ጥቁር ሆኖ አመዳም ቀለም የያዘ ቀልብ ናቸው።"» ሑዘይፋ እንዲህም አለ፡ «ለዑመር በአንተ እና በፈተናዋ መካከል የተዘጋ በር አለ። ልትሰበርም ትቀርባለች ብዬ ነገርኩት። ዑመርም "አላህ ያጠንክርህና ይሰበራል ማለት ነው? ቢከፈትስ ድጋሚ ሊዘጋ ይችላልን?" አለ። እኔም አይ እንደውም ይሰበራል። ንግግሬ ምንም ስህተት የሌለው መሆኑንና ያ በር ማለት የአንድ ሰውዬ መገደል ወይም መሞት እንደሆነ አስረግጬ ነገርኩት።» አቡ ኻሊድ እንዲህ አለ: «ለሰዕድ እንዲህ አልኩት "የጠቆረ አመዳም ቀለም ማለት ምን ማለት ነው?" ሰዕድም "ከጥቁረት ጋር የተቀላቀለ ንጣት ነው።" አለኝ። "የተዘነበለ ባልዲ ማለትስ" አልኩት። እርሱም "የተገለበጠ ማለት ነው።" አለኝ።»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ከኔ በኋላ ለወንዶች ከሴት የበለጠ እጅግ ጎጂ ፈተና አልተውኩም።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ ዝንባሌው ይዤ የመጣሁትን እስከሚከተል ድረስ አላመነም።"
ነወዊይ ሐዲሡ ሰሒሕ ነው ብለዋል በኪታቡል ሑጃ ሶሒሕ በሆነ ሰነድ ዘግበነዋል
"አላህ የቀጥተኛውን መንገድ ምሳሌ አደረገ። በቀጥተኛው መንገድ ዳርና ዳር ሁለት አጥር (ግድግዳ) አሉ፤ አጥሮቹ ዘንድ የተከፈቱ በሮች ይገኛሉ፤ በሮቹ ላይም የተለቀቁ መጋረጃዎች አሉ፤ በመንገዱ በር ላይ "ሰዎች ሆይ! ሁላቹም ወደቀጥተኛው መንገድ ግቡ እንዳትጣመሙ!" የሚል ተጣሪ አለ። ከቀጥተኛው መንገድ ከላይ ሆኖ የሚለፍፍ አንድ ተጣሪ አለ ፤ ከነዛ በሮች አንዱን መክፈት የፈለገ ጊዜ "ወዮልህ እንዳትከፍተው! ከከፈትከው ትገባለህ!" ይለዋል። ቀጥተኛው መንገድ ኢስላም ነው፤ ሁለቱ አጥሮች የአላህ ድንበሮች ናቸው፤ የተከፈቱት በሮች የአላህ ክልከላዎች ናቸው፤ ከቀጥተኛው መንገድ አናት ላይ የሚጣራው የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከቀጥተኛው መንገድ ከላይ ሆኖ የሚጣራው በሁሉም ሙስሊም ቀልብ ውስጥ የሚገኝ የአላህ መካሪ ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።