Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 4 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
«አንድ ሰውዬ ወደ አላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ በመምጣት እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንድ ሰው ገንዘቤን ለመውሰድ ፈልጎ ቢመጣ እስኪ ንገሩኝ ምን ላድርግ?" እርሳቸውም "ገንዘብህን እንዳትሰጠው" አሉት። እርሱም "ከተጋደለኝስ?" አላቸው። እርሳቸውም "አንተም ተጋደለው።" አሉት። እርሱም "ቢገለኝስ?" አላቸው። እርሳቸውም "አንተ ሰማዕት ነህ።" አሉት። እርሱም "ብገለውስ?" አላቸው። እርሳቸውም "እርሱ እሳት ውስጥ ነው።" አሉት።»
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ!" ሶሓቦችም: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ምን ናቸው?" ብለው ጠየቁ፥ ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በአግባቡ ካልሆነ በስተቀር መግደል፣ አራጣ መብላት፣ የየቲምን ገንዘብ መብላት፣ ጦርነት በተፋፋመ እለት ማፈግፈግ፣ ከዝሙት ዝንጉ የሆኑ ጥብቅ ምእመናትን በዝሙት መዝለፍ ናቸው።" አሉ።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
'ወንጀላቸውን ይፋ ከሚያደርጉ በስተቀር ሁሉም ህዝቦቼ ይማርላቸዋል። ይፋ ከማውጣትም መካከል ሰውዬው ምሽት ላይ አንድ ወንጀልን ይሰራል ከዚያም አላህ ለርሱ (ወንጀሉን) ሸሽጎለት አንግቶ ሳለ ‹እከሌ ሆይ! ትናንት ምሽት እንዲህ እንዲህ ሰራሁ።› ይላል። ጌታው (ወንጀሉን) ሸሽጎለት አድሮ ሳለ የአላህን ግርዶሽ ከራሱ ላይ የሚገፍ ሆኖ ያነጋል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ነፍሱን ከተራራ ላይ ጥሎ የገደለ ሰው በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ ሲምዘገዘግ ይኖራል። መርዝ ጠጥቶ ነፍሱን የገደለ ሰው በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ መርዙን በእጁ ይዞ ሲጠጣው ይቆያል። ነፍሱን በስለት የገደለ ሰውም በጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪና ዘላለማዊ በሆነ መልኩ ስለቱን በእጁ ይዞ ሆዱን እየወጋበት ይኖራል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።