Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 6 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
«አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ ትንሳኤ እለት ጠየቃቸው። "ትንሳኤ መቼ ነው?" አላቸው። እርሳቸውም "ለርሷ ምን አዘጋጅተሀል?" አሉት። እርሱም "እኔ አላህና መልክተኛውን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመውደዴ ውጭ ምንም ነገር አላዘጋጀሁም።" አለ። እርሳቸውም "አንተ ከወደድካቸው ጋር ነህ።" አሉት። አነስም እንዲህ አሉ፦ "በዚህ "አንተ ከወደድካቸው ጋር ነህ።" በሚለው የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ንግግር እንደተደሰትነው በምንም አልተደሰትንም።" ቀጥሎም (አነስ) እንዲህ አሉ: "እኔ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና)፣ አቡበከርንና ዑመርን እወዳለሁ። እነርሱ የሰሩትን አምሳያ ባልሰራ እንኳ እነርሱን በመውደዴ ከነርሱ ጋር መሆንን ተስፋ አደርጋለሁ።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሁለት ሙስሊሞች በሰይፋቸው (ሊጋደሉ) የተገናኙ ጊዜ ገዳዩም ሆነ ተገዳዩ እሳት ውስጥ ናቸው። " እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህ ገዳይ ሆኖ (እሳት መግባቱ መልካም) ተገዳዩ (እሳት የሚገባው) በምን ጥፋቱ ነው?" አልኩ። እርሳቸውም "እሱ ባልደረባውን ለመግደል ጉጉ ስለነበር ነው።" አሉ።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንዳችሁ ከወላጆቹ ፣ ከልጁና ከሰዎች ባጠቃላይ እርሱ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ እኔ እስክሆን ድረስ አላመነም።'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የበሽታ (በራሱ) መተላለፍ የለም፣ ገድም የለም፣ የጉጉት ድምፅ (ተፅእኖም) የለም፣ የሰፈር ወር ገደቢስነትም የለም። ከአንበሳ እንደምትሸሽው ከቁምጥና ወረርሽኝም ሽሽ!"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ስራዎች (ተቀባይነታቸው የሚለካው) በኒያ ብቻ ነው። ማንኛውም ሰው የሚመነዳውም ባለመው ኒያ ልክ ብቻ ነው። ስደቱ ወደ አላህና ወደ መልዕክተኛው ብሎ የሆነ ሰው (ምንዳውም) ለአላህና ለመልእክተኛው ሆኖለታል፤ የዱንያን ጥቅም ለማግኘት ወይም ሴትን ለማግባት ብሎ የተሰደደ ሰውም የስደቱ (ምንዳ) ለተሰደደለት ጉዳይ ነው።"»
ሶሒሕ ነው። ሁለቱ የሐዲሥ ሊቃውንት ኢማሞች (መሪዎች) አቡ ዐብዲላህ ሙሐመድ ቢን ኢስማዒል ቢን ኢብራሂም ቢን አል-ሙጊራህ ቢን በርዲዝበህ አል-ቡኻሪ እና አቡል ሑሰይን ሙስሊም ቢን አል-ሐጃጅ ቢን ሙስሊም አል-ቁሸይሪይ አን-ነይሳቡሪይ ከተጻፉት መጻሕፍት ሁሉ ይበልጥ ትክክለኛ በሆኑት በሁለቱ ሰሒሕ መጻሕፍቶቻቸው ውስጥ ዘግበውታል።
"ስራዎች የሚለኩት በኒያ (በሀሳብ) ብቻ ነው። ሰውየው የሚያገኘው ያሰበውን ነው። ስደቱ ወደ አላህና መልክተኛው የሆነ ሰው የስደቱ (ምንዳም) ወደ አላህና መልክተኛው ነው። ስደቱ ለዱንያ ጥቅማጥቅም ለማግኘት ወይም ሴትን ለማግባት የሆነ ሰው የስደቱ (ምንዳ) ወደ ተሰደደበት ነገር ወደዛው ነው።" በቡኻሪ ዘገባ ደግሞ፦ "ስራዎች የሚለኩት በኒያዎች (በሀሳብ) ብቻ ነው። ሁሉም ሰው የሚያገኘው ያሰበውን ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።