Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 5 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"በዝናባማና በድቅድቅ ጨለማ ምሽት የአላህ መልክተኛን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኛን እንዲያሰግዱን ፈልገን ወጣን። አገኘኋቸውና 'በል!' አሉኝ። ምንም አላልኩኝም። ቀጥለውም 'በል!' አሉኝ። ምንም አላልኩኝም። አሁንም 'በል!' አሉኝ። እኔም ምን ልበል? አልኳቸው። እርሳቸውም 'ሱረቱል ኢኽላስ እና ሁለቱን መጠበቂያዎች (ሱረቱል ፈለቅና ሱረቱን-ናስን) ስታመሽና ስታነጋ ሶስት ጊዜ ካልክ ለሁሉም ነገር ይበቁሃል።' አሉኝ።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።
‹ሶስት ጊዜ 'ቢስሚላሂለዚ ላየዱሩ መዐስሚሂ ሸይኡን ፊልአርዲ ወላፊስሰማእ ወሁወስ'ሰሚዑል ዐሊም' (ትርጉሙም: በዚያ ከስሙ ጋር በምድርም ይሁን በሰማይ ምንም ነገር የማይጎዳ በሆነው እንዲሁም ሰሚና አዋቂ በሆነው አላህ ስም።) ያለ ሰው እስኪነጋ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም። በሚያነጋ ጊዜም ሶስት ጊዜ ያላት ሰው እስኪያመሽ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም።› አባን ቢን ዑሥማንን የግማሽ አካል ሽባነት አገኘውና ከርሱ ይሄን ሐዲሥ የሰማው ሰውዬም አተኩሮ ተመለከተው። አባንም ለርሱ እንዲህ አለው: እንደዚ አተኩረህ የምታየኝ ምን ሆነው ነህ? በአላህ እምላለሁ! በዑሥማን ላይ ምንም አልዋሸሁም! ዑሥማንም በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ምንም አልዋሸም። ነገር ግን ዛሬ የደረሰብኝ ነገር የደረሰው ተቆጥቼ ስለነበር ይህን ዚክር ማለት ረስቼ ስለነበር ነው።"»
ሶሒሕ ነው። አቡዳወድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"የምህረት አጠያየቅ (የኢስቲግፋር) አለቃ 'አልላሁመ አንተ ረቢ ላ ኢላሃ ኢላ አንተ፣ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱክ፣ ወአነ ዓላ ዐህዲከ ወወዕዲከ ማስተጦዕቱ፣ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማ ሶነዕቱ፣ አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፣ ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ ፈግፊር ሊ፣ ፈኢነሁ ላየግፊሩዝ-ዙኑበ ኢላ አንተ።' ማለትህ ነው።'" እንዲህም ብለዋል "በርሷ አምኖ ቀን ላይ ያላትና በዛው ቀን ከማምሸቱ በፊት የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ባለቤቶች ነው። በርሷ አምኖ ምሽት ላይ ያላትና ከማንጋቱ በፊት የሞተ ሰውም እርሱ ከጀነት ባለቤቶች ነው።" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ፈጥረሀኛል እኔም ባሪያህ ነኝ፣ እኔ በቻልኩት መጠን በቃል ኪዳንህ ላይ እገኛለሁ፤ ከሰራሁት ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ፣ በኔ ላይ የዋልከውን ፀጋ አረጋግጣለሁ፣ ወንጀሌንም ላንተ አረጋግጣለሁና ማረኝ! እነሆ ካንተ በቀር ወንጀሎችን የሚምር የለምና።)
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
«ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሱብሒን የሰገዱ ጊዜ እርሷ መስገጃዋ ላይ ሆና ሳለ በማለዳ ከርሷ ዘንድ ወጡ። ከዚያም ከረፈደ በኋላ እርሷ (መስገጃዋ ዘንድ) ተቀምጣ ሳለ ተመለሱ። እንዲህም አሏት "እስካሁን ቅድም በነበርሸረበት ሁኔታ ላይ ከመሆን አልተወገድሽም?" እርሷም "አዎን" አለች። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሏት "ከአንቺ ጋር ከተለያየሁ በኋላ ሶስት ጊዜ አራት ንግግሮችን ተናግሬያለሁ። እነዚህ አራት ንግግሮች አንቺ ከንጋት ጀምሮ ካልሻቸው ጋር ቢመዘን (የኔ አራቱ ቃሎች) ሚዛን ይደፋሉ።" ሱብሓነሏህ ወቢሐምዲሂ፣ ዐደደ ኸልቂሂ፣ ወሪዷ ነፍሲሂ፣ ወዚነተ ዐርሺሂ ወሚዳደ ከሊማቲህ" አሏት።» ትርጉሙም "አላህ የፈጠራቸውን ፍጡራን ቁጥር ያህል፣ የነፍሱ ውዴታን ያህል፣ ዐርሹ የሚመዝነውን ያህል፣ የንግግሩ መጠን ያህል ከምስጋና ጋር ጥራት ይገባው።" ማለት ነው።
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"በምሽት ውስጥ የመጨረሻዎቹን የበቀራህ ምእራፍ ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው ይበቁታል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።