Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 5 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
«የትንሳኤ ቀን በሰዎች መካከል መጀመሪያ የሚፈረደው ጉዳይ የደም ጉዳይ ነው።»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'አላህ ዘንድ እጅግ ትልቁ ወንጀል ምንድነው?' ብዬ ጠየቅኩ። እርሳቸውም 'አላህ ፈጥሮህ ሳለ ለርሱ ቢጤን ማድረግክ ነው።' አሉ። እኔም 'ይህማ ትልቅ ነው።' አልኩኝ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'ልጅህን ከአንተ ጋር መብላቱን ፈርተህ መግደልክ ነው።' አሉኝ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'በጎረቤትህ ሚስት ላይ ዝሙት መስራትህ ነው።' አሉኝ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዷን ተናገሩ እኔ ደግሞ ሌላዋን ተናገርኩ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: ‹ ከአላህ ውጪ ሌላን ቢጤን (ባላንጣን) እየተጣራ የሞተ ሰው እሳት ገባ።› እኔ ደግሞ: ‹ለአላህ ሌላን ቢጤን (ባላንጣን) ሳይጣራ የሞተ ሰው ጀነት ይገባል።› አልኩኝ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
እውነተኛና (ይዘውት በመጡትም ሁሉ) እውነተኛ የተባሉት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም (ይህንን) ነገሩን፦ "የአንዳችሁ ፍጥረት በእናቱ ሆድ ውስጥ ለአርባ ቀንና ምሽት ይሰበሰባል። ከዚያም የዛኑ ቀናት አምሳያ የረጋ ደም ይሆናል፤ ከዚያም የዛኑ ቀናት አምሳያ ቁራጭ ስጋ ይሆናል፤ ከዚያም ወደርሱ መልዐክ ይላካል ፤ መልዐኩ አራት መልእክቶች ይታዘዛል፤ ሲሳዩን፣ የሞት ቀጠሮውን፣ ስራውንና እድለቢስ ወይም እድለኛ መሆኑን ይጽፋል። ከዚያም በውስጡ ነፍስ ይነፋበታል። አንዳችሁ በርሱና በጀነት መካከል የክንድ ያህል ርቀት እስኪቀር ድረስ የጀነት ሰዎችን ስራ ይሰራል። በርሱ ላይ የተጻፈው መጽሐፉ (ውሳኔ) ይቀድምና የእሳት ባለቤቶችን ስራ ይሰራና እሳት ይገባል። አንዳችሁ በርሱና በእሳት መካከል የክንድ ያህል ርቀት እስኪቀር ድረስ የእሳት ሰዎችን ስራ ይሰራል። በርሱ ላይ የተጻፈው መጽሐፉ (ወሳኔ) ይቀድምና የጀነት ባለቤቶችን ስራ ይሰራና ጀነት ይገባል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
“አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ፡- " የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ (ከእርሶ መላክ በፊት ባለው የድንቁርና ዘመን) በሠራነው ሥራ እንቀጣለን?" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉት፡- "በኢስላም ሥራውን ያሳመረ፥ በጃሂሊያ በሠራው ሥራ ተጠያቂ አይሆንም። እስልምናን ተቀብሎም መጥፎ የሠራ ግን በቀድሞውም በኋለኛውም ስራው ይጠየቅበታል። "
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።