Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 4 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
ኢብኑ ዓባስ ለዐጧእ ቢን አቢ ረባሕ እንዲህ አሉ:«ከጀነት ሰዎች መካከል የሆነች ሴት አላሳይህምን?" እኔም "እንዴታ!" አልኩኝ። እርሳቸውም እንዲህ አሉኝ: "ይህቺ ጥቁር ሴት ናት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች: ‹እኔ የሚጥል በሽታ አለብኝና እገላለጣለሁ። እንዲፈውሰኝ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም: ‹ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለሽ። ከፈለግሽ ደሞ ጤናን እንዲለግስሽ አላህን እለምንልሻለሁኝ።› አሏት። እርሷም ‹እታገሳለሁ።› ብላ እንዲህም አለች: ‹እኔ እገላለጣለሁኝ። እንዳልገላለጥ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም ዱዓ አደረጉላት።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁለት ቀብሮች በኩል አለፉና እንዲህ አሉ ' እነርሱ እየተቀጡ ነው። (በናንተ እይታ) ትልቅ በሆነ ወንጀልም አይደለም የሚቀጡት። አንደኛቸው ከሽንት አይጥራራም ነበር። ሌላኛው ደግሞ ነገር በማመላለስ የሚዞር ነበር።' ቀጥለውም እርጥብ ቅጠል በመያዝ ለሁለት ሰነጠቁትና በእያንዳንዱ ቀብር ላይ አንድ አንድ ተከሉ። ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለምን ይህን ፈፀሙ?' ብለው ጠየቁ። እርሳቸውም ‘ቅጠሎቹ እስካልደረቁ ድረስ ከነርሱ ላይ ቅጣቱን ያቀልላቸዋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።' ብለው መለሱ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሙዐዝ ቢን ጀበልን ወደ የመን በሚልኩበት ጊዜ እንዲህ አሉት፡ ' አንተ የመጽሐፍ ባለቤት ወደሆኑ ህዝቦች ትሄዳለህ። ስለዚህም እነርሱ ዘንድ ስትደርስ ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን ወደ መመስከር ጥሪ አድርግላቸው። እነሱ ለዚህ ጥሪህ ታዛዥ ከሆኑ አሏህ በነሱ ላይ በቀንና ምሽቱ ሁሉ አምስት ሶላቶችን ግዴታ እንዳደረገባቸው አሳውቃቸው። ለዚህ ጥሪህም ታዛዥ ከሆኑ አላህ በነሱ ላይ ከሀብታሞቻቸው ተይዞ ወደ ድሆቻቸው የምትሰጥ ምፅዋት ግዴታ እንዳደረገባቸው አሳውቃቸው። ለዚህ ጥሪህም ታዛዦች ከሆኑ አደራህን ውድ የሆኑ ንብረቶቻቸውን (ገንዘቦቻቸውን) ተጠንቀቅ! የተበዳይንም ልመና ተጠንቀቅ! እነሆ በሷና በአላህ መሀል ግርዶሽ የለምና።'"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከተከበረውና ከላቀው ጌታቸው በሚያስተላልፉት (ሐዲሠል ቁድሲይ) እንዲህ አሉ፦ አላህ እንዲህ አለ፦ "አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን ፅፏል ከዚያም ይህንን አብራርቷል። አንድን መልካም ስራ (ለመስራት) ያሰበና ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳን ይጽፍለታል ። እሱ (ለመስራት) አስቧት ከሰራት ደግሞ አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ (ከዛም አልፎ) እስከ ብዙ እጥፍ ድርብ የሚደርስ ምንዳዎች ይጽፍለታል። አንድን ኃጢዐት (ለመስራት) ያሰበና ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳ ይጽፍለታል። እሱ (ለመስራት) ካሰባትና ከሰራት አላህ ለሱ አንዲት ኃጢዐት ይጽፍበታል።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።