Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 27 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
«ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጋር ጉዞ ላይ ነበርኩ። አንድ እለት እየተጓዝን ሳለ ወደርሳቸው ቀረብኩኝና እንዲህ አልኳቸው: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጀነት የሚያስገባኝና ከእሳትም የሚያርቀኝን ስራ ንገሩኝ?" እርሳቸውም " በርግጥም ስለ ትልቅ ጉዳይ ነው የጠየቅከኝ፤ ጉዳዩ አላህ በርሱ ላይ ላቀለለለት ሰው ቀላል ነው። አላህን ልትገዛና በርሱ ላይ ምንንም ላታጋራ፤ ሶላትን ቀጥ ልታደርግ (በአግባቡ ልትሰግድ)፤ ዘካን ልትሰጥ፤ ረመዳንን ልትጾም፤ የአላህንም ቤት ሐጅ ልታደርግ ነው።" አሉና ቀጥለውም እንዲህ አሉ: "የመልካም ነገሮችን በር አልጠቁምህምን? ጾም ጋሻ ነው፤ ውሃ እሳትን እንደሚያጠፋው ሁሉ ምፅዋትም ወንጀልን ታጠፋለች፤ የሰውዬው በሌሊቱ አጋማሽ የሚሰግደው ሶላት" አሉና ቀጥለው {ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ስፍራዎች ይራራቃሉ} ከሚለው {ይሰሩትም በነበሩት} እስከሚለው ድረስ [ሱረቱ ሰጅዳ: 16‐17] አነበቡ። ቀጥለውም "የነገሩ ሁሉ ራስ፣ ምሰሶውንና ሻኛውን ልንገርህን?" አሉ። እኔም "እንዴታ የአላህ መልክተኛ ሆይ!" አልኳቸው። እርሳቸውም "የነገሮች ሁሉ ራስ (ዋና) እስልምና ነው፤ ምሰሶው ሶላት ነው፤ ሻኛው ጂሃድ ነው።" አሉ። ቀጥለውም "ይህን ሁሉ የሚቆጣጠረውን ነገር ልንገርህን?" አሉ። እኔም "እንዴታ የአላህ ነቢይ ሆይ!" አልኳቸው። ምላሳቸውን ያዙና "በራስህ ላይ ይህቺን ቆጥባት!" አሉ። እኔም "የአላህ ነቢይ ሆይ! እኛ በምንናገረው እንያዛለንን?" አልኳቸው። እርሳቸውም "እናትህ ትጣህና ሙዓዝ ሆይ! ምላሳቸው ያጨደችው ካልሆነ በቀር ሰዎችን በፊታቸው ወይም በአፍጢማቸው እሳት ውስጥ የሚደፋቸው (ሌላ ነገር) አለ እንዴ?" አሉኝ።»
ከሁሉም ሰነዶቹ አንፃር ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"አማኝ የሆነ ወንድና ሴት በርሱ ላይ ምንም ወንጀል የሌለበት ሆኖ አላህን እስኪገናኝ ድረስ በነፍሱ፣ በልጁና በገንዘቡ ላይ መከራ ከመከሰት አይወገድም።"»
ሐሰን ነው። ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"የዚህ ሃይማኖት ጉዳይ ቀንና ምሽት የደረሰበት ስፍራ ሁሉ ይደርሳል። አላህ፤ በሀያሉ ሀይልም ይሁን በውርደታሞች ውርደት ይህንን ሃይማኖት እያንዳንዱ የግንብ (የከተማ) ቤት ውስጥም ይሁን የሳር ቤት (የገጠር ቤት) ውስጥ ሳያስገባው አይቀርም። ወይ አላህ በርሱ ኢስላምን የበላይ በሚያደርግበት ሀይል አልያም አላህ በርሱ ክህደትን በሚያዋርድበት ውርደት (ኢስላም የበላይነቱን ይጎናፀፋል)።"» ተሚም አድዳሪም እንዲህ ይል ነበር "ይህንንም በወገኖቼ አወቅኩት። ከወገኖቼ የሰለሙት መልካምን፣ ልቅናና ክብርን አገኙ። ከወገኖቼ መካከል የካዱትንም ውርደት፣ የበታችነትና ግብር አገኛቸው።"
ሶሒሕ ነው። አሕመድ ዘግበውታል።