Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 19 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"(በአማና) በአደራ የማለ ሰው ከኛ አይደለም።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ቀን በመካከላችን ቆሙና በርሷ ምክንያት ልቦናዎች የራዱበት፣ ዓይኖች ያነቡበትን ጥግ የደረሰን ምክር መከሩን። 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! የመከሩን ምክር የተሰናባች ምክር ሆኖብናልና ለእኛ የሚሰጡን አደራ አለን?' ተባሉ። እርሳቸውም ' አላህን በመፍራት፤ የሐበሻ ባሪያ እንኳ ቢሆን (መሪያችሁን) እንድትሰሙና እንድትታዘዙ አደራ እላችኋለሁ። ከኔ በኋላ ከባድ ልዩነትን ታያላችሁ፤ ስለሆነም በኔ ሱናና የተመሩ ቅን በሆኑት ምትኮቼ ሱና አደራችሁን! እርሷን በማኘኪያ ጥርሳችሁ ነክሳችሁ ያዙ! አደራችሁን አዳዲስ መጤ ነገሮችን ተጠንቀቁ! ሁሉም ቢድዓ (አዲስ መጤ) ጥመት ነውና።' አሏቸው።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
«ከበኒ ዓሚር ልዑካን ጋር ወደ አላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሄድኩ። 'አንተ አለቃችን የሆንክ!' አልን። እርሳቸውም 'የሁሉም አለቃው አላህ ነው።' አሉ። እኛም 'በደረጃ በላጫችን እጅግ ታላቅ የሆንክ!' አልን። እርሳቸውም 'የምትሉትን በሉ ወይም ከምትሉት ከፊሉን በሉ ሰይጣን (ወደ ወሰን ማለፍ እንዳይጎትታቹ) አይጫወትባችሁ' አሉ።»
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።
"ለተቸገረ (ባለዕዳ) ጊዜ የሰጠ ወይም ይቅር ያለ አላህ ከጥላው በስተቀር ጥላ በሌለበት የትንሳኤ ቀን ከዐርሹ ጥላ ስር ያስጠልለዋል።"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"አሏህ ሆይ! ቀብሬን ጣኦት አታድርግብኝ፤ የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው በያዙ ህዝቦች ላይ የአሏህ እርግማን ሰፈነባቸው።"
ሶሒሕ ነው። አሕመድ ዘግበውታል።
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ ሑነይን የወጡ ጊዜ 'ዛቱ አንዋጥ' በምትባል የአጋርያን ዛፍ በኩል አለፉ። በርሷ ላይ (በረከትን በመፈለግ) መሳሪያዎቻቸውን ያንጠለጥሉባት ነበር። ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ለነርሱ ‹ዛቱ አንዋጥ› እንዳላቸው ለኛም (የምናንጠለጥልበት) ‹ዛቱ አንዋጥ› አድርግልን።' አሉ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ 'ለአላህ ጥራት ተገባው! ይህ (የተናገራቹት) የሙሳ ህዝቦች {ለእነርሱ አማልክት እንዳላቸው ለእኛም አምላክን አድርግልን።} [አል አዕራፍ: 138] ብለው እንደተናገሩት ነው። ያ ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታዬ እምላለሁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች መንገድ ትከተላላችሁ።'"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"አላህ ከሻ (ከፈለገ) እና እከሌ ከሻ (ከፈለገ)' አትበሉ። ይልቁንም 'አላህ ከሻ (ከፈለገ) ከዚያም እከሌ ከሻ (ከፈለገ)' በሉ።"
ከሁሉም ሰነዶቹ አንፃር ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ነሳኢ በኩብራ ውስጥ፣ አሕመድ ዘግበውታል።
'በኛና በነርሱ (በከሀዲዎች) መካከል ያለው (መለያ) ቃል ኪዳን ሶላት ነው። ሶላትን የተወ ሰው በርግጥም ክዷል።'"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ፣ ነሳኢ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።