Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 6 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
“የአንድ ሰው እስልምናው ያማረ ለመሆኑ ምልክቱ የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው።"
ነወዊይ ሐዲሡ ሐሰን ነው ብለዋል ቲርሚዚይና ሌሎችም ዘግበውታል
"ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ!" ሶሓቦችም: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ምን ናቸው?" ብለው ጠየቁ፥ ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በአግባቡ ካልሆነ በስተቀር መግደል፣ አራጣ መብላት፣ የየቲምን ገንዘብ መብላት፣ ጦርነት በተፋፋመ እለት ማፈግፈግ፣ ከዝሙት ዝንጉ የሆኑ ጥብቅ ምእመናትን በዝሙት መዝለፍ ናቸው።" አሉ።
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አደራችሁን ጥርጣሬን ተጠንቀቁ! ጥርጣሬ እጅግ ውሸት የሆነ ወሬ ነውና። አትፈላፈሉ፣ አትሰልሉ፣ አትመቀኛኙ፣ ጀርባም አትሰጣጡ፣ አትጠላሉ (ይልቁንም) የአላህ ባሮች ሆይ! ወንድማማቾች ሁኑ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ሆነ ብሎ በኔ ላይ የዋሸ ሰው ከእሳት የሆነ መቀመጫውን ያዘጋጅ።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የአላህ ፊት የሚፈለግበትን እውቀት የዱንያን ጥቅም ለማግኘት ካልሆነ በቀር ለሌላ ግብ የማይማረው ከሆነ የትንሳኤ ቀን የጀነትን ሽታ አያገኝም።"»
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
"ድሃ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም: "እኛ ዘንድ ድሃ ማለት ዲርሀምና መጠቃቀሚያ እቃ የሌለው ሰው ነው።" አሉ። እርሳቸውም: "በኡመቴ ውስጥ ድሃ ማለት የትንሳኤ ቀን ሶላት፣ ፆም፣ ዘካ ይዞ የሚመጣ ነው። ነገር ግን ሲመጣ ይህንን ሰድቧል፣ ይህንን በዝሙት ዘልፏል፣ የዚህን ገንዘብ በልቷል፣ የዚህን ደም አፍስሷል፣ ይህንን መትቷል። ለዚህኛውም (ለተበዳዩ) ከመልካም ስራው ይሰጠዋል። ለዚያኛውም ከመልካም ስራው ይሰጠዋል። በርሱ ላይ ያለበት ሀቅ ተፈርዶ ሳይጠናቀቅ መልካም ስራው ካለቀ ደሞ ከነርሱ ወንጀል እየተወሰደ በርሱ ላይ ይጫንበትና ከዚያም እሳት ውስጥ ይጣላል።" አሉ።
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።