Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 9 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"ከወንድሙ ክብር የተከላከለ ሰው በትንሳኤ ቀን አላህ እሳትን ከፊቱ ይከላከልለታል።"
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
"ሙእሚን የሆነ ሰው እጅግ ተቺ፣ እጅግ ተራጋሚ፣ ፀያፍ ተግባር ሰሪ፣ መጥፎ ንግግር ተናጋሪ አይደለም።"»
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ ዘግበውታል።
«"ወደኔ ተወዳጅ የሆነውና የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ወደኔ ቅርብ የሚሆነው መልካም ስነምግባር ያለው ነው። ወደኔ የተጠላውና የትንሳኤ ቀንም መቀመጫው ከኔ እጅግ የራቀው እውነትን ለመቀልበስ እየተጣጣረ የሚያወራ፤ ለአንደበተ ርቱእነት ንግግር የሚያበዛና ሙተፈይሂቆች ናቸው።" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እውነትን ለመቀልበስ እየተጣጣረ የሚያወራንና ለአንደበተ ርቱዕነት ንግግር የሚያበዛን አውቀናል። መተፈይሂቆች እነማን ናቸው?" አሉ። እርሳቸውም "ኩራተኞች ናቸው።" አሉ።»
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ ዘግበውታል።
"የትንሳኤ ቀን ከመልካም ስነ ምግባር የበለጠ የአማኝን ሚዛን የሚደፋ አንድም ነገር የለም። አላህ ፀያፍ የሚሰራንና ፀያፍ የሚናገርን ይጠላል።"
ሶሒሕ ነው። አቡዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።
"ከፀያፍ ቃላትም ይሁን ድርጊት የራቁ ነበሩ፤ በየገበያው የሚጮሁም አልነበሩም፤ መጥፎንም በመጥፎ የሚመልሱ አልነበሩም። ይልቁንም መጥፎን ይቅርታ በማድረግና ችላ ብሎ በማለፍ ነበር የሚመልሱት።"»
ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
'ከአማኞች መካከል ኢማናቸው የተሟላው ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ የሆኑት ናቸው ፤ ከአማኞች መካከል ምርጦቹ ደግሞ ለሴቶቻቸው ምርጥ የሆኑት ናቸው።'"
ሐሰን ነው። አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአብዛኛው ሰዎችን ጀነት ስለሚያስገባው ነገር ተጠየቁ፤ እሳቸውም "አላህን መፍራት እና መልካም ስነምግባር ነው።" አሉ። በአብዛኛው ሰዎችን እሳት ስለሚያስገባቸው ነገርም ተጠየቁ። እሳቸውም "ምላስና ብልት ነው።" አሉ።
ሐሰኑን ሶሒሕ ነው። ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።