Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 5 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"አላህ ወንጀሎችን የሚሰርዝበትን፣ ደረጃዎችን ከፍ የሚያደርግበትን ነገር አልጠቁማችሁምን?" ሶሐቦችም "እንዴታ የአላህ መልክተኛ" አሉ። እርሳቸውም "በአስቸጋሪ ወቅት ዉዱእን አዳርሶ ማድረግ፣ ወደ መስጂድ እርምጃ ማብዛት፣ አንድ ሰላት ካለቀ በኋላ ሌላ ሶላት መጠበቅ፤ ይኸው ነው "ሪባጥ" (ዘብ መጠበቅ) ናቸው።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንድ ሰውዬ እየሄደ ሳለ መንገድ ላይ እሾካማ ቅርንጫፍ አገኘና አራቀው። አላህም ስራውን ተቀበለው። ወንጀሉንም ማረው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ትላልቅ ወንጀሎችን ከተጠነቀቀ አምስቱ ሶላቶች፣ ከጁሙዐ እስከ ጁሙዐ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው የተሰሩትን ወንጀሎች ያስሰርዛሉ።"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።
"ቤቶቻችሁን መቃብር አታድርጉ! ቀብሬንም የሚጎበኝ የበአል ስፍራ አታድርጉት! ይልቅ በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ! የትም ብትሆኑ ሶለዋታችሁ ትደርሰኛለችና።"
ሐሰን ነው። አቡዳውድ ዘግበውታል።
"ፀጉረ ጨብራራና ከበር ተገፍትሮ የሚባረር በአላህ ሲምል ግን አላህ ከመሃላው የሚያጠራው ስንትና ስንት ሰው አለ?!"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።