Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 103 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ

ዘጋቢ

ሁሉንም ዘጋቢዎች አሳይ (46)
"አብዛኛው ሰው በነርሱ የከሰረባቸው ሁለት ፀጋዎች አሉ: ጤንነትና ነፃ (ትርፍ) ወቅት"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህቺን አንቀፅ አነበቡ {እርሱ ያ በአንተ ላይ መጽሀፉን ያወረደ ነው። ከእርሱ (ከመፅሀፉ) ግልጽ የሆኑ አንቀጾች አሉ። እነሱ የመጽሐፉ መሠረቶች ናቸው። ሌሎችም ተመሳሳዮች አሉ። እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች ማሳሳትን በመፈለግና ማጣመምን በመፈለግ ከርሱ የተመሳሰለውን ይከታተላሉ። (ትክክለኛ) ፍቺውንም አላህ ብቻ እንጂ ሌላ አያውቀውም። በዕውቀትም የጠለቁት "በርሱ አምነናል፤ ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው" ይላሉ። የአእምሮ ባለቤቶችም እንጅ (ሌላው) አይገሰጽም።} [ኣሉ ዒምራን: 7] ቀጥለው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፦ " እነዚያ ከቁርኣን የተመሳሰለውን የሚከተሉትን ከተመለከትሽ አላህ ተጠንቀቁዋቸው ብሎ የጠቀሳቸው እነሱ ናቸው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የምትረዱትና የምትቀለቡት በደካሞቻችሁ ሰበብ አይደለምን?"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
"ከጀሀነም ነዋሪዎች መካከል እጅግ ዝቅተኛ ቅጣት የሚቀጣው ለርሱ ሁለት የእሳት ጫማዎችና የጫማ ማሰሪያዎች የሚደረግለት ነው። በነርሱም ምክንያት ድስጥ እንደሚንፈቀፈቀው አንጎሉ ይንፈቀፈቃል። ከርሱ የበለጠ ቅጣት የሚቀጣ አንድም ሰው አለ ብሎም አያስብም። እርሱ እየተቀጣ ያለው ግን እጅግ ዝቅተኛውን ቅጣት ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንድ ሰው በአንድ ሰው ቀብር በኩል እያለፈ 'ዋ ምኞቴ ምናለ በርሱ ስፍራ ላይ እኔ በነበርኩ!' እስኪል ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ትናንሽ ተደርገው የሚታዩ ወንጀሎችን ተጠንቀቁ! የትናንሽ ወንጀሎች ምሳሌ ወደ አንድ ሸለቆ እንደወረዱ ሰዎች ምሳሌ ነው። ይሄም አንድ እንጨት ይዞ ሲመጣ፤ ያም አንድ እንጨት ይዞ ሲመጣ ምግባቸውን (አቀጣጥለው) መጋገር እንደቻሉ ሰዎች ነው። ትናንሽ ወንጀሎች (የሚሰራውን) ባለቤት ባስያዙት ጊዜ መጥፊያው ይሆናሉ።"»
ሶሒሕ ነው። አሕመድ ዘግበውታል።
"የሽማግሌ ቀልብ ለሁለት ነገሮች ወጣት ከመሆን አይወገድም: (እነርሱም) ዱንያን በመውደድና ምኞትን በማርዘም ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
"መስካችሁ ላይ ሙጥኝ አትበሉ ዱንያን ትከጅላላችሁና።"»
በሌላ ምክንያት ሐሰን የሆነ (ሐሰን ሊገይሪሂ) ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።