Skip to content
777 ሐዲስ

የነብዊ ሐዲሶች ኢንሳይክሎፒዲያ

ውጤቶችን አጣራ

ከ777 92 ካርዶች

ማጣሪያዎችን አጥፋ
"የምትረዱትና የምትቀለቡት በደካሞቻችሁ ሰበብ አይደለምን?"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
"ከጀሀነም ነዋሪዎች መካከል እጅግ ዝቅተኛ ቅጣት የሚቀጣው ለርሱ ሁለት የእሳት ጫማዎችና የጫማ ማሰሪያዎች የሚደረግለት ነው። በነርሱም ምክንያት ድስጥ እንደሚንፈቀፈቀው አንጎሉ ይንፈቀፈቃል። ከርሱ የበለጠ ቅጣት የሚቀጣ አንድም ሰው አለ ብሎም አያስብም። እርሱ እየተቀጣ ያለው ግን እጅግ ዝቅተኛውን ቅጣት ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"አንድ ሰው በአንድ ሰው ቀብር በኩል እያለፈ 'ዋ ምኞቴ ምናለ በርሱ ስፍራ ላይ እኔ በነበርኩ!' እስኪል ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"ትናንሽ ተደርገው የሚታዩ ወንጀሎችን ተጠንቀቁ! የትናንሽ ወንጀሎች ምሳሌ ወደ አንድ ሸለቆ እንደወረዱ ሰዎች ምሳሌ ነው። ይሄም አንድ እንጨት ይዞ ሲመጣ፤ ያም አንድ እንጨት ይዞ ሲመጣ ምግባቸውን (አቀጣጥለው) መጋገር እንደቻሉ ሰዎች ነው። ትናንሽ ወንጀሎች (የሚሰራውን) ባለቤት ባስያዙት ጊዜ መጥፊያው ይሆናሉ።"»
ሶሒሕ ነው። አሕመድ ዘግበውታል።
"የሽማግሌ ቀልብ ለሁለት ነገሮች ወጣት ከመሆን አይወገድም: (እነርሱም) ዱንያን በመውደድና ምኞትን በማርዘም ነው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪ ዘግበውታል።
"የአደም ልጅ ሁለት በገንዘብ የሞላ ሸለቆ ቢኖረው ኖሮ ሶስተኛ ሸለቆ ይመኛል። የአደምን ልጅ ሆድ ከአፈር በቀር የሚሞላው የለም። ወደ አላህ ተፀፅቶ በተመለሰ ሰው ላይም አላህ ተውበቱን ይቀበለዋል።"»
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"የምድራችሁ እሳት ከጀሀነም እሳት ሰባ ክፍል አንዷ ክፍል ናት።" "የአላህ መልክተኛ ሆይ! (የምድር እሳት ለቅጣት) በቂ ነበረች’እኮ" ተባሉ። እሳቸውም፦ "የጀሀነም እሳት ከምድር እሳት በስልሳ ዘጠኝ ክፍል እንድትበልጥ ተደርጋለች። ሁሉም ክፍል የምድር እሳት አምሳያ ሀሩርነት (አቃጣይነት) ነው ያላቸው።"
ሶሒሕ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
"በሁሉም ውስጥ መልካም ነገር ቢኖርም፤ ጠንካራ ሙእሚን ከደካማው ሙእሚን አላህ ዘንድ የተሻለና ይበልጥ ተወዳጅ ነው። በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ! በአላህም ታገዝ! አትስነፍ! አንዳች ነገር ሲያገኝህም ‹እንዲህ አድርጌ በነበር እንዲህ እንዲህ ይሆን ነበር።› አትበል። ይልቁንም ‹ይህ የአላህ ውሳኔ ነው። የሻውንም ፈፀመ።› በል። (እንዲህ ቢሆን ኖሮ) ማለት የሰይጣንን ስራ ትከፍታለችና።'"
ሶሒሕ ነው። ሙስሊም ዘግበውታል።